top of page

ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች

 

 

ላፈቀርካት ሴት ያለህን የፍቅር ስሜት እንዴት መግለፅ ትችላለህ?

·          

·          

ከቅድስት አባተ
ፍቅርም ሆነ መፈቃቀር ለሰው ልጆች በሙሉ ያለመድልዎ የተሰጠ ፀጋ ነው፡፡ ፍቅር የሁላችንም አካል ነው፡፡ በፍቅር የተሞላና የተሻለ የፍቅር ኑሮ እንዲኖረንም የብዙዎቻችን ምኞት ነው፡፡ ታዲያ የእኛው ሆኖ ሳለ ብዙዎቻችን ፍቅርን አንቀበለውም ወይም እናባርረዋለን፡፡ ፍቅርንመ ሰጥተን እንዳንቀበል ብዙዎቻችን ማዕቀብ የተደረገብን ይመስለናል፡፡ ፈላጊና ተፈላጊ ሳይገጣጠሙ ሲቀሩ ደግሞ ፍቅር እንደተራብን ልንቆይ ግድ ይለናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የፍቅር ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚገደዱት ወንዶች በመሆናቸው ይህን የፍቅር ስሜት ለመግለፅ በህይወታቸው ውስጥ ትልቁ የቤት ስራ ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን የፍቅር ስሜታችንን ለመግለፅ የሚኖረን አካሄድ ከልጅነት አስተዳደጋችን ጋር ተያይዞ የሚመጣና ውስጣችን ተቀርፆ ባለው መልኩ ለፍቅር በደረስንበት ዕድሜ ላይም እንደ ችግር ወይም በተቃራኒው እንደ ጥሩ ነገር ልናንፀባርቀው እንችላለን፡፡
ለዚህም ነው አስቀድመን ፍቅር የሚለውን ቃል ራሱ ስናስብ በአዕምሯችን ሀሳባዊ የሆነ ነገር እንስላለን፡፡ እዘህ ላይ ልናይ የሚገባን ነገር ልጆች እያለን ምንም የምንስለው ሀሳባዊ ነገር በፍቅር ዙሪያ ስላልተነገረን ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ብቻ ከዕድገት ለውጣችን ጋር በሚፈጠረው ፍቅር ልባችንን ክፍት አድርገን እንቀበላለን፤ ለማጣጣምም እንሞክራለን፡፡ በሀሳባዊ ስዕል ውስጥ በቅፅበት የሳልነውን ፍቅር ለማግኘት ደግሞ ስለሚከብደን እየተፈቀርን እንኳን ፍቅርን እንራባለን ወይም እያፈቀርን እንኳን የተፈቃሪን ልብ ማግኘት ያስቸግረንና ፍቅርን እንራባለን፤ ያለመገጣጠም ማለት ይህ ነው፡፡ እንደ ልጅነታችን ቢሆን ኖሮ እኮ ሰዎች ትኩረት ስለሰጡን ወይንም ልናገኘውና የእኛ ልናደርገው የምንፈልገውን ነገር አንድ ሰው ሲያደርግልን የፍቅር ስሜቱ በቀላሉ ይገባና ተፈቀርን ብለን እናስብና የፍቅር ረሃባችንን እናስወግድ ነበር፡፡ ያ ማለት ትኩረት የሰጠን ወይንም የምንፈልገውን ነገር የሰጠን ሁሉ አፍቃሪያችን እንደሆነ እናስብ ነበር ማለት ነው፡፡ ታዲያ አድገን የእኛ እንዲሆን የምንፈልገው ፍቅር እንደ ልጅነታችን ከብዙዎች መምጣቱን ሳይሆን እኛው ካፈቀርነው ሰው ብቻ ምላሹን መጠበቃችን ሁለቱን የተለያዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ለማፍቀር በደረስንበት ዕድሜ ወቅት አፍቅሮ እንዲፈቀሩ መፈለግ ወይም ለፍቅር መጠያየቅ ተፈጥሯዊ እንደሆነ ማወቅ የግድ የሚሆነው፡፡ እንደ ተፈጥሮነቱ ፍቅርን ስንፈልግ ደግሞ የህይወት አጋርን የመፈለግ ጉዞ ውስጥ እንገባለን፡፡ በዚህ የመፈላለግ ጉዞ ውስጥ ታዲያ የሁለቱም ተፈላላጊዎች መገጣጠም ይኖርና ነገሩ ቀላል ሊሆንላቸው ይችላል፡፡ ለአንዳንዶቹ ደግሞ ፈላጊው ራሱ አፍቃሪ ይሆንና ተፈቃሪዋ ብዙም መፈቀሯን ሳታውቅ በፍለጋ ብቻ ረዥም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይህ በተለይ ወንዶች ላይ በብዛት የሚንፀባረቅ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ምክንያት ደግሞ በብዙ ልማዶችና እምነቶች የፍቅር ጥያቄን ማቅረብ ያለበት ወንድ ነው የሚል እሳቤ ሰርጾ ስለነበር ነው፡፡ ይህ አመለካከት በተወሰነ መልኩ የተቀየረ ቢሆንም በብዛት ግን አሁንም ሴቷ እያፈቀረችውም ቢሆን የፍቅር ጥያቄው ከወንዱ እንዲመጣ የመፈለግ ዝንባሌ አለ፡፡ ይህን ሁኔታ ወንዶች አቅልለውት በመመልከት ፍቅራቸው የሚበልጥባቸው ከሆነ ፍርሃታቸውን አስወግደው የፍቅር ጥያቄያቸውን አስወግደው የፍቅር ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ከተሳካላቸው እኮ ከሴቷ የበለጠ የአሸናፊነት ስሜት የሚሰማቸው ወንዶቹ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ረዥሙን ሂደት የተጓዙትና ድል ያደረጉት እነሱ ናቸውና፡፡ ታዲያ ወንዱ ከራሱ የፍቅር ስሜት በመነሳትና ውስጡን በማዳመጥ ይጀመርና ማንነቷን ከለየ በኋላ እንዴት ፍቅሩን ሊገልፅላት እንደሚችል ማወቅ አለበት፡፡
ገና ስታያት ልብህ የደነገጠላትን ሴት እንደምንም ብለህ ማናገር አለብህ፡፡ በደንብ ለመግባባት እንድትችሉ ደግሞ በተቻለህ አቅም መንገድ ላይ እየሄዳችሁ ከሆነ የተገናኛችሁት መንገድህን ቀይረህ ከእሷ ጋር በመሄድ ጨዋታችሁን አራዝም፣ በታክሲም ውስጥ ከሆነም እንዲሁ መንገድህን አሳልፈህ በመሄድ በተቻለህ አቅም በደንብ ለመግባባት የሚያስችላችሁን ረዘም ያለ ወሬ በማውራት ተጨዋወቱ፡፡ ስትለያዩም ሌላ ጊዜ እንድትገናኙ ስልክ ቁጥሯን ተቀበላት፡፡ አንድ ሶስት ቀን በስልክ ከተገናኛችሁ በኋላ አንድ የእረፍት ቀን ተገናኝታችሁ ሻይ ቡና እንድትሉ ጠይቃት፡፡ በመቀጠልም የምትገናኙበትን እያንዳንዷን ቀን ከፋፍላቸውና ማንነቷን በደንብ የምታውቅበት አንተም ማንነቷን የምትገልፅበት የፍቅርንም ስሜት የምትረዳበት አድርጋቸው፡፡ እነዚህን በግንኙነታችሁ ተከታታይ ቀናት ምን እንደሚመስሉ እናያቸዋለን፡፡
1. የመጀመሪያ ቀን ግንኙነት
የመጀመሪያ ቀን ስትገናኙ ስለ ስራዋ፣ በስራ ቦታና ስላጋጠማት ነገር፣ ስለ ቤተሰቦቿ እናም ከፍቅር ውጭ ስለሆኑ ሌሎች ጉዳዮች አንስታችሁ ተወያዩ፡፡ በመጀመሪያ ግንኙነታችሁ ከፍቅር ውጭ በተለመዱ ጉዳዮች ላይ መነጋገራችሁ ሳትጨናነቁ ዘና ብላችሁ እንድታወሩ ይረዳችኋል፡፡ ስታወሩ ታዲያ በደረቁ ሳይሆን የተለያዩ ቀልዶችን እያነሳህላት አስቃት፡፡ በጨዋታ የታበ ቆይታችሁ ደስ የሚል ጊዜን እንድታሳልፉ ከማድረጉም በላይ አንተ የማታጨናንቅ ቀለል ያልክ ሰው እንደሆንክ ስለምትረዳ እሷም ነፃነቷን ያገኘች ያህል እንዲሰማትና እንድትጫወት ታደርጋታለህ፡፡ እዘህ ጋር መጠንቀቅ ያለብህ ነገር ከእሷ የበለጠ ብዙ አታውራ፣ ለእሷ ሰፊውን ጊዜ ስጣትና አንተ ብዙውን ጊዜ አድማጭ ሆነህ ተገኝ፡፡ የሚያዳምጣትን ሰው በማግኘቷ በጣም ደስ ይላታል፤ ለአንተም ቦታና ክብር ትሰጥሃለች፡፡ ይህን ማድረጋችሁ ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን እሷም ካንተ ጋር በድጋሚ ተገናኝታ የምታወጉበትን ቀጣይ ቀን እንድትናፍቅር ያደርጋታል፡፡ ስለ ቀጣይ የመገናኛ ቀናችሁም ትንሽ ተባባሉ፡፡ ነገር ግን የግድ በዚህ ቀን ካልሆነ ብላችሁ አትወስኑ፡፡ መደዋወል እንደምትችሉ ተማምናችሁ ተለያዩ፡፡ ስትለያዩ ቢቻል እስከተወሰነ መንገድ ዎክ እያደረጋችሁ ብትሄዱ ወይም ቤቷ ልትደርስ ግማሽ መንገድ እስኪቀራት ድረስ አብራችሁ በታክሲም ብትሄዱ፤ ያለበለዚያ በትራንስፖርት አሳፍረሃት ብትመለስ የመሳሰሉትን እንደ አማራጭና እንደ ሁኔታዎች እያየክ መፈፀም ከቻልክ አንድ ትልቅ ማህተም መተህ እንደላካት ልትቆጥር ይገባሃል፡፡
2. የሁለተኛ ጊዜ ግንኙነት
በስልክ ጥሩ የሆኑ አስደሳች ንግግሮችን ካደረጋችሁ በኋላ ብዙም ሳትርቁ ለሁለተኛ ጊዜ የምትገናኙበትን ቀን ተነጋግራችሁ ተቀጣጠሩ፡፡ ታዲያ ለሁለተኛ ጊዜ ለመገናኘት ስትቀጥራት እንደመጀመሪያ ጊዜያችሁ አነስ ያለ ቦታ ወይም ካፌም ሳይሆን ሬስቶራንት ቢሆን የምትጋብዛትም ሻይ ቡና ሳይሆን ምሳ ወይም እራት መሆን አለበት፡፡ ስትገናኙ አለባበሷንና ስብዕናዋን ሁሉ አድንቅላት፡፡ ታዲያ አንተም የራስህን ስብዕና የሚጠብቁ አለባበስና አቀራረብ ይዘህ ተገኝ፡፡ ጋባዡ አነተ ብትሆንም የምትፈልገውን ነገር እንድታዝ ነፃነቷን ስጣት፣ ካላወቀችውም አሪፉን ነገር አስረዳትና የተሻለውን እንድትመርጥ አድርጋት፡፡ በዚህ ቀን የሚኖራችሁን ሰፊ ሰዓት ስለግል ሕይወታችሁ በስፋት በማውራት እየተጨዋወታችሁ አሳልፉ፡፡ በግንኙነታችሁ መቀራረብ ውስጥ ውስጧንም እያጠናህ መሄድህን እንዳትረሳ፡፡ የበላችሁት የጠጣችሁት ነገር እንደተመቻት ጠይቃት ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልግ ከሆነም እንድታዝ አድርግ፡፡ የሁለተኛ ቀን ውሎዎቹ በጥሩ ሁኔታ ከተጠናቀቁ በድጋሚ ሌላ ቀን ለመገናኘት እንደምትቀጣጠሩ አሳውቃት፡፡ የምትቀጣጠሩ ቀን ግን ከተለያያችሁበት ጊዜ በጣም የረዘም መሆነ የለበትም፡፡ ያሳለፋችሁት ጣፋጭ የሆኑ ጊዜያቶች ከአዕምሯችሁ ብዙም ሳይጠፋ ሳትርቁ ለመገናኘት ሞክሩ፡፡ ታዲያ ቀጠሯችሁ ከተሳካ አሁንም በሬስቶራንት ውስጥ መሆኑን ተነጋገሩ፡፡ ወጪ ለመቀነስ ብለህ ወደኋላ ተመልሰህ ካፌ ውስጥ ወይም የወረደ ቦታ ለመቀጣጠር አትሞክር፡፡ ከእንግዲህ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ የሚያስብልህ ምንም ነገር የለም፡፡ የዚህን ቀን ውሏችሁን አጠናቃችሁ ከመለያየታችሁ በፊት ወንድ እንደመሆንህ ነገሮች ከአንተ አፍ ቅድሚያ ይጠበቃሉና በቆይታችሁ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍህን ንገራት፡፡ እሷን በማግኘትህና አንተን አክብራ ከአንተ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሆና በመገኘቷ በጣም ደስ እንዳለህም አሳውቃት፡፡ እሷን ሁሌ ብታገኛት እንኳን እንደምትደሰት ንገራትና ቶሎ ቶሎ እንደምትደውልላት በመግለፅ ለወደፊቱ ስሜትህን በቀላሉ ለመግለፅ እንዲያመችህ ዳር ዳር ማለት ትጀምራለህ፡፡ እንደተለመደው ከሸኘሃት በኋላ በንጋታው ደውልላት ትናንተ በጣምጥሩ ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ንገራት የእሷንም ስሜት ጠይቃትና ቀጣዩ ስራህን ፍቅር ፍቅር እያሰኘህ ለማስኬድ ልታስብበት ተዘጋጅ፡፡
3. የሶስተኛ ቀን ግንኙነት
በዚህ ጊዜ ዕድለኛ ከሆንክ ራሷ ደውላ ባለፈው ጥሩ ጊዜ እንዳሳለፈች ገልፃልህ በድጋ እንድትገናኙ ትጠይቅሃለች፡፡ ይህን ካደረገች ጥልቅ የሆነ ስሜት በውስጧ እንደተፈጠረባት ያሳያል፡፡ ለአንተም የምትመችህ አይነት ሴት መሆኗን ካረጋገጥክ የፍቅር ጥያቄውን ማቅረብ ቀላል ሊሆንልህ ይችላል፡፡ በዚህ ወቅት ምንም ነገር አላለችም ማለት ግን ምንም ስሜት የላትም ማለት አይደለም፡፡ አሁንም ስሜቷን ለመግለፅ ተቆጥባ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ስልክ ደውለህ ካነጋገርካት በኋላ ስሜቷን ስላልገለፀች መክፋትህን ሳታስነቃ ሌላ ቀን እንደምትደውልልለት ነግረህ ተሰነባበታት፡፡ በተቻለ አቅም ለሶስተኛ ጊዜ እንድትገናኙ እንደምትፈልግ ራሷ እስክምትገልፅልህ ድስ ስልክ እየደወልክ ብቻ ጠብቅ፡፡ ነገር ግን ስሜቷን እንድትገልፅ ፈፅሞ መገፋፋት የለብህም፡፡ ምክንያቱም ከተነቃብህ ውስጧ ቶሎሊረበሽ ይችላልና እንዳማረህ ይቀራል እንጂ ትንፍሽ አትልልህም፡፡ ከዚህም አልፎ ይህ የችኩልነት ባህሪ ሊያስጠላት ይችላል፡፡ ሶስተኛው ቀን በጣም ወሳኝ እንደሆነ አስብና በስልክ ደስ የሚሉ ወደ ፍቅር የሚያመሩ ወሬዎችን በቀልድ መልክ አውራት፡፡ በሞባይልም ከሆነ ደስ የሚሉ ፍቅርን ሊጠቁሙ የሚችሉ ነገር ግን በጣም ፍቅርን በግልፅ የሚያሳዩ ሆነው ያላፈጠጡ መልዕክቶችን (SMS) ላክለት፡፡
የእሷ መልስ ላይ ብዙ ትኩረት አታድርግ ወይም አትጠባበቅ፡፡ የሶስተኛው ቀን ግንኙነታችሁ በስልክ ረዥም ሰዓትን የወሰደ ከሆነ ከላይ በተገለፀው መልኩ ነገሮችን ግለፅላት፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ጠብቀህ ካልሳካልህ በቀጣይ ቀናት ራስህ እንድትገናኙ ትቀጥራትና በሌላ ጊዜ ደግሞ እሷ እንድትቀጥርህ እድል ስጣት፡፡ በዚህ ቀን ስትገናኙ ግን ሆን ብለህ ወሬያችሁ ሁሉ በፍቅር ዙሪያ ብቻ እንዲሆን በማድረግ ያላትን ስሜት ለማወቅ ሞክር፡፡ ላንተ የፍቅር ስሜት እንዳላት ከሁኔታዋ ለማወቅ ከቻልክ አንተም ያለህን ስሜት ዳር ዳር እያልክ ግለፅላትት፡ ለምሳሌ ከሰውነቷ ክፍል ፀጉርሽ ወይም ጥርስሽ ያምራል እያልክ፣ የፊትሽ ቆዳ ደግሞ እንዴት ይለሰልሳል እያልክ እየነካካሃት ግለፅላት፡፡ ስሜቷ ግልፅ ካልሆነልህ ግን በቀጥታ በጣም የፍቅር ሰው እንደሆነችና አንተም እንደወደድካት በመግለፅ ያላትን ስሜት እንድትነግርህ ጠይቅ፡፡ ምላሹ እሷም እንደምታፈቅርህ ከገለፀች ፍለጋህ ተሳክቷል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በቀጥታ ደስ የሚል የፍቅር ሽሚያ ውስጥ የሚያስገባችሁን መንገድ ልትከተሉ ትችላላችሁ፡፡ ለምላሿ ጊዜ የምትፈልግ ከሆነም ጊዜ ስጣት ምላሿ ግን ከአንተ ጋር በፍቅር መቆየት እንደማትፈልግ ወይም ሌላ በፍቅር የምትወደው ጓደኛ ካላትና ለእሱ የምትሰጠውን ፍቅር ለአንተ መስጠት የማትችል ከሆነ በዚሁ የፍቅር ፍለጋህን ልታቆም ይገባል፡፡ ከዚህ በላይ እርግጠና ያልሆንከውን ነገር ይዘህ በመጓዝ ጊዜህን ማባከንም ሆነ ከማትሆንህ ሴት ጋር በመኳተን ጭንቀት ውስጥ በመግባት ህይወትህን ከምታበላሽ በጊዜው መፍትሄ ስጠው፡፡ አንተንም የምትብቅ ለአንተ የታሰበችና የተቀመተች ሌላ ሴት ልትኖር ትችላለችና ይህቺ ሴት እየጠበቀችህ ነውና እሷን ብዙ ማስቆም የለብህም፡፡ የሕይወትህን አቅጣጫ ቀይረውና ሌላ ሙከራ ውስጥ ግባ!

 

 

 

 

ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች

 

የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!!
አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡


ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ
አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡


- ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡
- ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡
- እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
- አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡
- በምታወሩበት ጊዜ ሁሉ በተለይ ደግሞ እሷ ስታወራ አንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች የምትነካህ ከሆነ መልካም ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አይኖቻችሁ በሚጋጠሙበት ጊዜም ምቾት የማይሰጥ ቢሆን እንኳን እንደተፋጠጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላይ መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር ፊትህን ከማዞርህ በፊት ፈገግ ማለትን ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ታዲያ የአንተ እሷን መውደድና መልካም ሰውነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እየሰረቀቸፍ ስታይህ ልታጋጥምህ ትችላለች፡፡ ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መገጣጠም በኋላ እንድታናግራት መፈለጓን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
እንደ መልካም ተጫዋችነትህ የጨዋታውን ህግ በማክበር የፈለገችውን ነገር ማሟላት ግድ ይልሃል፡፡
መሽከርከር፡- አንድ ሴት ፀጉሯን አየር ላይ ወርውራ ወዲያው ዞራ ካየችህ አንተ እንድታያት ለማድረግ እየጣረች መሆኑን ማመን ትችላለህ፡፡


ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴዎች
በማንኛውም ሁኔታ ስትመለከታት አይኗን ውስጡን የምታሽከረክረው ከሆነ በአንተ አቀራረብ ማፈሯንና እንዲሁም በአንተ ደስተኛ አለመሆኗን ለሰዎች ለማሳየት እየጣረች መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ ይህ ነገር ከተፈጠረ እሷን የማግኘት እድልህ ትንሽ በመሆኑ ማድረግ ያለብህ ፊትህን አዙሮ መሄድ ነው፡፡


- በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡


ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡


የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች
አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡


ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ መረጃዎች
1. ፀጉር ማፍተልተል
አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡
2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር


በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡
3. በክንዷ ስትደገፍ
አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?›› ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች ብዙ ጊዜ ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሚፈልጉት በዚህ መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ መልሱ ምን እንደሆነ አንተ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ እረጋ በማለትና በቀልድ በማዋዛት ውሳኔዋን ልታስቀይራት ትችላለህ፡፡


4. እጇን በማጣመር ተደግፋ ስትቀመጥ
ይህ አጋጣሚ በጭፈራ ቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴት በማደን ላይ ከሆንክና ካጋጠመህ ዕድለኛ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ያለች ሴት ሁኔታህ አልተመቻትም ወይም አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡


5. ከንፈሯን ስታረጥብ
አንድ ሴት ከአንተ ጋር እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡ የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር የለብኝም፡፡


6. ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ
ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡


7. እግር ማወዛወዝ
እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡ በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/ ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡


8. የጣቶች አይነት
አንድ ሴት ለእጇ ያላት አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷን መረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/ ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት ይሻላል፡፡


9. ከንፈሯን ከበላች
በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ አይን አፍጥጠህባት ይሆን?


10. ነፍሷን አዳምጠው
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡


ጮክ ብላ የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣ እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች ከተኳኳለችና ሽቶ ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡  source:-

ደስተኛ ለመሆን ትፈልጋላችሁ? እነዚህን 20 አመለካከቶች ቀይሩ

ደስተኛ ሰዎች እያንዳንዱ እርምጃቸው ላይ በራስ መተማመን ይታያል፡፡ የሚናገሩትን ነገር የሚያደርጉት ይመስላል፡፡ የትኛውም ስፍራ ሲገኙ ዙሪያ ገባውን በአስደሳች ስሜት መሙላት ያውቁበታል፡፡ ደስተኛ ሰዎች ህይወትን በደስታ እያጣጣሙ መኖር የሚችሉበትን ምስጢር የደረሱበት ይመስላል፡፡

የእነዚህ ሰዎች ደስታ ምስጢር በአመዛኙ ከአንዳንድ አይነት ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማህበረሰቡ ‹‹ይሄ ብቻ ነው ልክ ብሎ›› ሙሉ እውቅና የሰጠውን ነገር እነርሱ ሌላ ልክ ነው ወይም የተሻለ ነው ብለው በሚያስቡት ልምድ የመተካት ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ ደስተኛ ሰዎች ደስተኛ ለመሆን ወደ ውጪ አይመለከቱም፡፡ ይልቁንም የውስጥ መሪ ኮምፓሳቸው ላይ እምነት ይጥላሉ፡፡

ደስታ ኮትኩተው ሊያሳድጉት የሚችሉት ነገር ነው፡፡ እናም ማህበረሰቡ ልክ ናቸው ብሎ ያጠመቀንን ልማዶች በገዛ ራሳችን የውስጥ ምሪት በተገኙ ልማዶች በምንተካበት ልክ ደስተኛ እንሆናለን፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 20 አመለካከቶች ኑሮ የሚባል ትምህርት ቤት ውስጥ ቀስመናቸዋል የምንላቸው ነገር ግን መለወጥ የሚገባቸው የህይወት አተያዮች ናቸው፡፡ መቀየር የሚጠበቅብንን እነዚህን አመለካከቶች እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡

1. አንድ ነገር የሚሰራበት ልክ እና ስህተት የሆነ መንገድ አለ፡፡
አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና የተለዩ ሂደቶችን መፈተሽ የዕድገት አካል ነው፡፡ ለአንድ ሰው የሚሰራ ነገር ለአንተ/ለአንቺ አይሰራ ይሆናል፡፡ የራሳችሁን እምነት እና የራሳችሁን ሂደት ፈልጉ እና እርሱን ተከተሉ፡፡ ሌሎችም እንዲሁ የራሳቸውን ፈልገው ይከተሉ፡፡
2. ሌሎችን መምሰል ህብረት መፍጠር ነው፡፡ ሌሎችን ለመምሰል ስንሞክር የራሳችን የውስጥ ፍላጎት ላይ እስር እናውጃለን፡፡ ሌሎችን ለመምሰል መሞከር ለራስ ታማኝ አለመሆን ነው፡፡ ሌሎችን ለመምሰል ከመጣር ይልቅ ከገዛ የውስጥ እና የእውነት ማንነታችን ጋር ለመሰለፍ፣ በአንድነት ለመቆም ጥረት ማድረግ ይበልጣል፡፡ በራሳችሁ መተማመን ስትጀምሩ እና በራሳችሁ ደስተኛ ስትሆኑ ከሌሎች ጋርም ራሳችሁን ሳታጡ የላቀ ግንኙነት እና ትብብር መፍጠር ትችላላችሁ፡፡
3. ጠንክሮ መስራት ስኬታማ ያደርጋል፡፡ ከልክ በላይ ትዝላላችሁ፡፡ በጥረታችሁ ያን ያህል አትደሰቱም፡፡ በጥንካሬ በመስራት ምትክ በብልሃት እንዴት መስራት እንደምትችሉ አስቡ፡፡ ስኬታችሁን በምታገኙት ደስታ መጠን መዝኑ፡፡
4. ውድቀት ክፉ ነገር ነው፡፡ መውደቅ ስለራሳችሁ ድንቅ ትምህርት የምትቀስሙበት መንገድ ነው፡፡ አንዳንድ ነገሮችን ሞክረን ሳይሳካልን ሲቀር ለምን ሊሳካልን እንዳልቻለ እና በቀጣይ ደግሞ ምን ምን ብናደርግ ስኬታማ መሆን እንደምንችል እንማራለን፡፡ አለማችን ላይ እጅግ በጣም የተሳካላቸው ሰዎች ብዙዎቹ ብዙ ጊዜ ወድቀው የተነሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ‹‹በቂ ውድቀት ውድቄያለሁ ወይ?››
5. ብቻችሁን ሆናችሁ ማለት ብቸኛ እንደሆናችሁ ትዘልቃላችሁ ማለት ነው፡፡ ከራሳችሁ ጋር በምትኑበት ወቅት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የምትችሉ ከሆነ ብቻችሁን የምትሆኑበት ጊዜ ያለ ምንም ጥርጥር መጠኑ እያነሰ ይመጣል፡፡
6. ህይወት አልጋ በአልጋ መሆን አለበት፡፡ የህይወት ከፍታና ዝቅታዎች ሚዛናዊ ህይወት የምንኖርበት መንገድ ነው፡፡ እያንዳንዱን ሂደት በፀጋ ተቀበሉ፡፡ ግብግብ መግጠማችሁን ስትተዉ ሰላም ማግኘት ትጀምራላችሁ፡፡
7. ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡት ነገር ወሳኝ ነው፡፡
ዋናው እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር እናንተ ስለ እናንተ የምታስቡት ነው፡፡ ከራሳችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ላይ ስሩ፡፡ ከአሰባችሁት በላይ ደስታ እና ፍቅር ይሰማችኋል፡፡
8. ቀጭን፣ ቆንጆ፣ ብልጥ፣ ሀብታም፣ ጤነኛ ብትኑ ኖሮ ደስተኛ ትሆኑ ነበር፡፡
ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ ያለ ነገር ላይ ደርሳችሁ ደስተኛ እንሆናለን ብሎ ማሰብ ከንቱ ድካም ነው፡፡ የምትፈልጉት የክብደት መጠን፣ የምትፈልጉት አይነት አፍቃሪ ግንኙነት፣ ፍፁም ለእናንተ የሚስማማ ስራ አግኝታችሁ ይሁን እንጂ ደስተኛ መሆን ያልቻላችሁት ምን ያህል ጊዜ ነው? ሁልጊዜ! ደስታ ከእኛ ውጪ የሚገኝ ነገር አይደለም፡፡ ይልቁንም እውስጣችን የሚገኝ ፈርጥ ነው፡፡
9. ህይወታችሁ ከመንገድ ዝንፍ ብሎ ወጥቷል፡፡
‹‹መድረስ ያለብኝ ቦታ አይደለም የደረስኩት›› አልያም ደግሞ ‹‹ህይወቴን እንደ አሰብኩት አይደለም እየመራሁ የምገኘው›› የሚል ሃሳብ ዛሬን በደስታ እንዳታሳልፉ እንቅፋት ይሆንባችኋል፡፡ የምትፈልጉት ቦታ ነው ያላችሁት፡፡ ሁሉም ነገር ያለ ምንም መዛነፍ እንደሚከናወን እመኑ፡፡
10. መተው መሸነፍ ነው፡፡
ወደ ታች የሚጎትታችሁን ነገር መተው ስኬት እና ደስታ የምታገኙበት አንድ አዲስ መንገድ ነው፡፡ ጥቅም እየሰጣችሁ ያልሆነን ነገር ስትተዉ ከልብ የምትፈልጉት ነገር ወደ ህይወታችሁ እንዲገባ በራችሁን ወለል አድርጋችሁ ከፈታችሁ ማለት ነው፡፡ ‹‹መተው ነገሬን ከተተው›› አደል ከነተረቱስ?
11. አልሆን ያለን ነገር መጠበቅ ጥሩ ነው፡፡
ከአዲስ እና እንግዳ ዓለም ጋር በስምምነት መኖርን እወቁበት፡፡ አልሳካ ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሁ የማናውቀውን መልዓክ ስለፈራን ብቻ የምናውቀው ሰይጣን ላይ ተጣብቀን መኖር የለብንም፡፡
12. ደስታን ለነገ፣ ለነገ ወዲያ ይደርስበታል ብሎ ማለፍ ያስፈልጋል፡፡
ጡረታ፣ የዓመት ረፍት፣ ቅዳሜ እና እሁድ ወዘተ… የምንላቸው ነገሮች በአሁኑ ሰዓት ደስታን ለአለማጣጣም በምክንያትነት የምንደረድራቸው ሰበቦች ናቸው፡፡ እያንዳንዱን ቀን በደስታ ለማሳለፍ ሞክሩ፡፡
13. ከልባችሁ ይልቅ ጭንቅላታችሁን መስማት አለባችሁ፡፡
ጭንቅላታችሁ አንዳንዴ ልክ እንደሆነ ከሚሰማችሁ ነገር ውስጥ ጎትቶ ያወጣችኋል፡፡ የልባችሁን ምሪት መከተል ስህተት አይደለም፡፡ ያላችሁበት የትኛውም አይነት ሁኔታ ልክ እንደሆነ ይሰማችሁ እንደሆነ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡
14. እንዴት እውን እንደምታደርጉት/እንደምታሳኩት ያላወቃችሁትን ነገር አትሞክሩ፡፡
ህልማችንን እንዴት ማሳካት እንደምንችል እግረ መንገዳችንን እንማራለን፡፡ ስለዚህ ሞክሩት፡፡ የወደፊቱ ማንነታችሁ (Future self) ያመሰግናችኋል፡፡
15. የማይተባበሯችሁ ሰዎች ስለ እናንተ ግድ የላቸውም፡፡
ሌሎች የሚናገሩት እና የሚሰሩት ነገር ከእናንተ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም፡፡ ይበልጥ በራሳችሁ እና በህልማችሁ መተማመን በጀመራችሁ መጠን ያን ያህል ሌሎች አመኑባችሁ አላመኑባችሁ ግድ አይሰጣችሁም፡፡
16. ራስን መውደድ ስህተት ነው፡፡
ለራሳችሁ መቆም ስትችሉ ነው ለቀሪው ዓለምም መቆም የምትችሉት፡፡ ሁሌም ቢሆን ፍቅርን ከራሳችሁ እንደጀመራችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ሙሉ ነገር ነው ለሌላውም የሚተርፈው፡፡
17. ህልማችሁን ወደ ጎን ተወት አድርጋችሁ ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ፡፡
ህልማችሁ ኃላፊነታችሁ ነው፡፡ በመሆኑም በረባ ባልረባ ሰበባ ሰበብ የነፍስ ጥሪያችሁን ቸል አትበሉ፡፡
18. መዳረሻው ነው ሽልማቱ፡፡
መድረስ የሚባል ነገር የለም፤ ሂደቱ እና ጉዞው ነው ሽልማቱ፡፡ ስለዚህ እመንገዳችሁ ላይ ሃሳባችሁን ሰብስባችሁ መገኘታችሁን አረጋግጡ፡፡
19. ምስጢርን ማካፈል የድክመት ምልክት ነው፡፡
የውስጥ ስሜታችሁን እና ሃሳባችሁን ለሌሎች ማካፈል ደስተኛ መሆን የምትችሉበት ምስጢር ነው፡፡ ስሜታችሁን ማካፈል ማለት ግልፅ መሆን እና ነገሮችን ለመሸፋፈን አለመጣጣር ማለት ነው፡፡ ግልፅነት አሁን የምትገኙበትን ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ መቀበል እና በኩራት ይህንን ማንነት ማንፀባረቅ ስራችሁ ነው፡፡
20. ማንነታችሁ ስራችሁ ነው፡፡
እናንተ ተውላጠ ስም አይደላችሁም፡፡ ከስራችሁ እና ከለት ተለት እንቅስቃሴያችሁ በላይ እጅግ የላቃችሁ ናችሁ፡፡ ሁሉን ነገር ማንነትንም ጨምሮ ከሥራ ጋር ማያያዝ ተገቢ አይደለም፡፡ ሥራችሁ የማንነታችሁ አንድ አካል እንጂ ማንነታችሁ አይደለም፡፡

ሴቶች ከወንዶች ማግኘት የሚፈልጓቸው 6 ነገሮች

ከሊሊ ሞገስ

ሴቶች በየዕለቱ በህይወታቸው ውስጥ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት በተለያየ መልኩ ይገለፃል፡፡ ከዚህም አልፎ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም እንዲሆን የእነሱንም ፍላጎት የሚመችና የሚያረካቸው እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ፡፡ እስከ ትዳር የሚዘልቁም ሆነ ከትዳር በፊት ከትዳርም ውጪ ቢሆን የራሳቸውን ሰብዕና ጥሩ በሆነ መልኩ እየገነቡ የሚያሳዩዋቸው ባህሪያትንና ፍላጎቶቻቸውን ወንዶች እንዲረዱላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ሴቶች የውስጣቸውን ፍላጎት የሚረዳላቸው ብቻ ሳይሆን ተቀራርቦ አብሯቸው ካለና ፍላጎታቸውን ከተረዳላቸው ወንድ ጋር ረዥም ጊዜ መቆየትንና ደስ የሚል ህይወትን መምራት ይፈልጋሉ፡፡

ከዚህም በላይ የእነሱን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ የሚንከባከባቸውንና የሚጠነቀቅላቸውን ወንድ አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡ ደስ ብሏቸው ከጥሩ ወንድ ጋር መልካም ህይወት ከጀመሩ በኋላ ፈፅሞ መራቅን አይመርጡም፡፡ አብሯቸው ጥሩ ግንኙነት ጀምሮ ወንዱ ሲርቃቸው ውስጣቸው በጣም ይጎዳል፡፡ ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡትን መልካም ግንኙነት እየጠሉትም ከወንዶች ጋር እንደገና ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት ይቸገራሉ ጥርጣሬ ውስጥም እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡

የጥናቱ አካል ከሆኑት መካከል ታዋቂዋ የጎልፍ ተጨዋች ሀና ራውሰን ስትናገር ‹‹በጣም የሚስብና ቆንጆ ነው ብዬ ካሰብኩት ወንድ ጋር ጥሩ የፍቅር ግንኙነት ጀምሬ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ከእኔ ጋር እየቆየ ሲመጣ እኔን የሚንከባከበኝ በመጥፎ ሁኔታ እየሆነ በመምጣቱ ልንለያይ ችለናል›› ብላለች፡፡ ንግግሯን ስትቀጥልም ‹‹በመለያየታችን ውስጤ ቢጎዳም ለሚቀጥለው ህይወቴ ብዙ ነገር እንድማርበትና ፍላጎቴን የሚጠብቅልኝን የተሻለ ወንድ ለማግኘት ይረዳኛል›› ስትል ነበር አስተያየቷን የገለፀችው፡፡

ራውሰን ቀጥላ ስትናገር ‹‹ወንዶች በጣም እንደማምርና ውብ እንደሆንኩኝ ይነግሩኛል፡፡ ለምን የምጫወተው የጎልፍ ጨዋታዬን እያዩም አያበረታቱኝም ትላለች፡፡ ውበቴን ቢያደንቁ የበለጠ ለውበቴ እንድጨነቅና እንዳምር ያደርገኛል እንጂ የጎልፍ ጨዋታ ውጤቴ ላይ የተሻለ ለውጥ እንዳመጣ አያደርገኝም፡፡ እኔ ሁሉን ፍላጎቴን እያደነቀና እያበረታታ ውስጤን የሚጠብቅልንን ወንድ ነው የምፈልገው፡፡ እነዚህን ፍላጎቶቼን አውቆ የበለጠ የሚጠብቅልን ሳገኝ ውጫዊው ሆነ ውስጣዊ ውበቴ እንዲጎላና የአካላዊም ሆነ የጭንቅላት ዝግጁነቴ ሙሉ ሆኖ ኮንፊደንስ ወይም በራስ መተማመን እንዲኖረኝ የማድረግ ኃይል ይኖረዋል›› ብላለች፡፡ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ስለሌሎቹ ስትጠቅስም፡፡

በዚህ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሁላችንም ሴቶች የበለጠ የምንስብ ውብ መሆንም እንችላለን፡፡ ወንዶች ይህን ከተረዱልንም የውስጣችንም ስሜትና ፍላጎት በቀላሉ ፈንድቶ እንዲወጣና እነሱንም የበለጠ በሚፈልጉት መልኩ ማርካት እንችላለን ትላለች የጎልፍ ተጨዋቿና ሞዴሊስቷ ራውሰን፡፡ ከዚህ በመነሳት የራሷን ልምድ በማካፈሏ በብዙ ሴቶች ላይ ያለውን ነገር ለማንፀባረቅ ችላለች፡፡ ራውሰን ስታክል ‹‹ወንዶች ልክ የምጫወትበትን የጎልፍ መምቻና እንቅስቃሴውን ይመስሉኛል፡፡ የጎልፍ መምቺያ ሁልጊዜ በሴቶችና በወንዶች መካክል መነሻ የሚሆነውን ፍላጎት የሚወክል ሲሆን ከመታውኝና ጥሩ ነጥብ ማስቆጠር የምችልበትን እንቅስቃሴ ሳደርግ ወንዶች የእኔን ፍላጎት ተረድተው አብረን እየተጓዙ ደስ የሚል ህይወት ውስጥ የምገባበት ሁኔታን ወክዬ አየዋለሁ›› ስትል ገልፃለች፡፡ በአጠቃላይ የሴቶችን ፍላጎት በመረዳትና ይህፍላጎታቸው የበለጠ ፈንድቶ እንዲወጣ የማድረግ ስራ የወንዶች ይሆናል እንደ ጥናቱ ገለፃ፡፡ ጥናቱ ወደ መጨረሻ የመደምደሚያ ሃሳብ ላይ ሲመጣም የሴቶችን ፍላጎት በመረዳት ወንዶች እንዴት ለበለጠ ጥሩ ግንኙነት እነሱን ማነሳሳት እንደሚችሉና የራሳቸው ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
እነዚህ የሴቶች ፍላጎት የበለጠ እንዲፈነዳና የራሳቸው እንዲሆኑ ከወንዶች የሚጠበቁና ሴቶቹን ወደ ራሳቸው ለማምጣትና ለመምራት የሚያስችሉ ጥለቅ የሆኑ ተግባሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ፍላጎቷን እስክታገኘው ደጋግመህ ጠይቅ

ብዙውን ጊዜ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደሆነ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ቶሎ የውስጣቸውን ፍላጎት ለማግኘት ስለሚቸገሩ ነው፡፡ በተለይም የሴቶች የውስጥ ፍላጎት ፈንድቶ እንዲወጣ ለማድረግ አስቸጋሪ ስሆነ ይህንን ለማድረግ ወንዶች በተለያየ አቅጣጫ ሴቶችን ደጋግመው መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ በጥያቄዎችህ ውስጥ መላመድህን እሷ እየወደደችው ስትመጣ ፍላጎቷን አውጥታ ትገልፅልሃለች፡፡ ሴቶች በብዙ ነገር ግንኙነት ውስጥ ስለሚፈሩና ስለሚጠነቀቁ ይህንን ተረዳው፡፡ ነካክቶ መተው ለአንተም ለእሷም ጥሩ አይደለም፡፡ ስለዚህም ጥንቃቄ ባለው መልኩ ሳታሰለቻት ደጋግመህ ለመጠየቅ ሞክር፡፡

2. ሴቶችን ወደተሻለ ደረጃ ለማምጣት ሞክር

ብዙ ሴቶች መልካምና ቀና የሚያስብላቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን እጅግ ሲበዛ ጀንትል ሆኖ የሚረጋጋ ወንድ አይመቻቸውም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሴቶች የውስጣቸውን እየተረዳቸው በጣም የሚያነቃቃቸውን እንዲሁም የሚፈልጉትን ቶሎ ተረድቶ እርካታን የሚሰጣቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም ወንዱ የተሻለ ደረጃ ላይ ሆኖ እነሱን የበለጠ የሚቆሰቁሳቸውና ትልቅ የንቃት ኃይል ወደ ውስጣቸው የሚጨምርላቸው እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የተሻለ ሆኖ ተገኘና የእነሱንም ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣትና የተሻለ ቦታ ላይ ለማምጣት ሞክር፡፡

3. ግንኙነትህን አጠንክረው

ወደ ፍቅር የሚሄደው ግንኙነትህ ያማረ እንዲሆን አስቀድመህ የእሷን ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣት ደጋግመህ መገናኘትን እንደ ጥሩ ዘዴ ተጠቀምበት፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እሷ ለአንተ በጣም እንደምታስፈልግህ እየነገርካት እንደሆነ እሷም ፍላጎቷን እንድታወጣውና እየገፋፋሃትና እያሳወቃት እንደሆነ ትረዳለች፡፡

4. ከሴቶች ጋር ማንኛውም ነገር ለማድረግ ባቀድከው መንገድ ተጓዝ፡፡

ለሴቶች ልታደርግላቸው አንድ ነገር ስታስብ ፕሮግራምህን አትሰርዝባቸው፡፡ ሴቶች በተለይም ወደ ጥሩ ግንኙነት እየመጡ ከሄዱ በኋላ የቀጠሮ ሰዓትም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ካሳወቃቸው በኋላ የምትሰርዝ ከሆነ ፍፁም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ሊበሳጩም ይችላሉ፡፡ አንተም ፍላጎቷን ለማግኘት የነበረክ ሂደት ላይ ውሃ እንደመከለስ ስለሚቆጠር ጥንቃቄ አድርግ፡፡ ፍላጎቷን እየመራህ ለመሄድ ፕሮግራሞችህ ወጥና የማይለወጡ ይሁኑ፡፡

5. በእሷ ላይ ጥሩ አቋም ወይም አስተያየት ይኑርህ

አንተ እንደ ወንድነትህ ሌላ እሷ የምትጠረጥረውን ነገር ባታደርገውም እንኳን ንገራት፡፡ ታማኝ መሆንህ ለእሷ ፍላጎት ጎልቶ መታየት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርግልሃል፡፡ ነገር ግን ጥሩነትህን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እየገለፅክ በእሷ ላይ ጥሩ የሆነ አቋም እንዳለህ ንገራት፡፡

6. ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ አስፈላጊ ንክኪዎችን ተጠቀም

ልክ እንደምታወሩትና እንደምትተያዩት ሁሉ ጥሩ የሆኑ የእጅ መነካካትና መጨባበጥ ብሎም በእጅህ ትከሻዋን እቅፍ እያደረክ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍን እንደ ትልቅ የፍላጎቷ ማውጫ መንገድ ተጠቀምበት፡፡ ከዚህም በላይ ጥንቃቄ የተሞላባቸው አስፈላጊ ንክኪዎች ሴቶችን በፍቅር የማሞቅ ከፍተኛ ኃይል አለው፡፡
በአጠቃላይ እነዚህን መሰረታዊ የጥናቱ የጨመረሻ ሃሳቦችን በመጠቀም ወንዶች የሴቶችን ፍላጎት በቀላሉ በመረዳትና ፈንድቶ እንዲወጣ በማድረግ ወደራሳቸው በማምጣት የሚፈልጓትንም በቀላሉ የራሳቸው በማድረግ ጥሩ ግንኙነት እንዲመሰረቱ ያደርጋቸዋል፡፡ አንተም ወንዱ ፍላጎቷን ጠብቅ ከዛም የበለጠ ራሷ አፈንድታው ትነግርሃለች፡፡ ያኔም የአንተ ትሆናለች፡፡ አንተም የእሷ ማለት ነው፡፡

እውነተኛ ፍቅርን የሚያጠናክሩ 5 ጠቃሚ ምክሮች

 

 

 

 

 

 

 

 

1. በቂ የአብሮነት ጊዜን ማሳለፍ

በፍቅር የተቆራኘን ጥንድነት በመፍጠር ከጥብቅ ትዳር የተሳሰረን ጎጆ መቀየስ የአብዛኛዎቹ ጥንዶች የቀን ተሌት ህልምና ምኞት ነው፡፡ የጥንዶች ህልም እውን የሚሆነውና ምኞታቸው የሚሰምረው የጥንድነት መተሳሰሪያውን በበቂ ጊዜ በማጥበቅ ከሁለቱም ጫፍ መደገፍ ሲቻላቸው ነው፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ አብይ ምሳሌ ከተጣመሩ ዘንድ የአብሮነትን ስሜት ለመዝራትና ጣፋጭ ፍሬውንም ለመቋደስ በቂ የአብሮነት ጊዜን መሰዋት ቀዳሚ ተግባራቸው መሆን እንዳለበት ይመክራል፡፡ በቂ ጊዜን መቸር መቻላቸው ለጥንድነታቸው ማዝገሚያ እርፍን፣ ለአብሮነት የአዝመራቸው ማሳን ስንክሳሩን መለያ (መውቂያ) አውድማውን እንዲሁም ለፍቅራቸው በቂ ስንቅንና ለትዳራቸው አስተማማኝ ጥረትን እንዲቋጥሩ ያግዛቸዋል፡፡
ስለዚህ ወረት ያላየውንና ጊዜ የማይሽረውን እውነተኛ ፍቅር ከሁለት በአንዱ ግንኙነት እጅ ለማስገባት ከሚሹ ሁሉ ወረት ያላየውንና ጊዜ የማይሽረውን በቂ ጊዜ ከምንም አስቀድመው (አስበልጠው) ከማንም ሰስተው (መስዋዕትነትን ከፍለው) ለጥንድነቱ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከግንኙነቱ የወረት ሳንካዎች መሀል የአብሮነትን ምስጢርና የጋራ ድርሻን በመዘንጋት በተናጥል ለመወጣት መሞከር አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ደግሞ የግል ፍላጎትን ከመሙላትና የራስን ፍትወተ ስጋ ብቻ ከማድመጥና ከመከተል ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ ለራስ ወዳድነት (Selfishness) ያጋልጣል፡፡ ከዚህም በላይ በጥምረት ለሚገፉን የጥንድነት አቀበትን ለብቻ ለመግፋትና ሸክሞቹንም ከአንድ ወገን ጫንቃ በመከመር እስከ የስነ ልቦና ችግሮች ድረስ ያደርሳል፡፡
በመሆኑም ከዚህ የፍቅር ጥምረት ጉዞ ላይ እያሉ ከመነሻው እስከ መድረሻው በመመካከርና ሀሳብ ለሀሳብ በመያያዝ (ልብ ለልብ በመተሳሰር) የልዩነት አቅጣጫዎችን ከመያዝ መውጣትና የተጣጣመና ቀላል ጉዞን በአብሮነት ጊዜ ውስጥ ማበጃጀት ይችላሉ፡፡

2. መራራውንም ጣፋጩንም ፅዋ በጥንድነት መጎንጨት

ጥንድነት በሁለትዮሽ የተገመደ የፍቅር አሀድ እንደመሆን አንድነቱ ጠቅልሎ የሚያስራቸውን ትሩፉቶች ብቻ ሳይሆን በአንድነቱ ተበትነው የሚፈቱ የእርካታ ችግሮችንም ማስተናገዱ አይቀሬ ነው፡፡ በተለይ ከዚህ የጥንድነት ጉዞ ጣልቃ የሚገቡና ፈታኝ መሰናክሎችን የሚጋርጡ ችግሮችን ጥንዶች ለየብቻቸው መጋፈጣቸው የአንድነቱ መፈተሻ ሆኖ በማገልገል ከአንደኛው ወገን የተለየ እክልን ይፈጥራሉ፡፡ እንግዲህ ይህን ጊዜ ነው የብዙ የስነ ልቦና ሐኪሞችን ቀልብ በገዛው የአብርሃም ማስሎ መርሆ የመመራትና አለመመራት ጉዳይ ትውስ የሚለን፡፡ የዚሁ እውቅ የስነ ልቦና ሐኪም መርህና አገላለፅ መሰረት በእንግሊዝኛው “Self-actual- evasion” በማለት ያስቀመጠውንና በአማርኛው ትርጉም ሲጠጋጋ ‹‹ከራስ በላይ ንፋስ፣ ከእኔ ወዲያ ለእኔ›› የመሳሰሉት የአኗኗር መፈክር ለጥንድነት የመለያያ መነሻ መንገድ ይሆናል፡፡ ይህን በእኔነት ተጀምሮ የእኔነት ማብቂያ የሌለውን የኑሮ ዘይቤ ወደ እኛነት ያልቀለበሱ ጥንዶች የጥንድነት ዕድሜ በባለሙያዎቹ ምክር ከአንዲት ጀምበር መድረሱ እንኳ አጠራጣሪ ነው፡፡ በጋራ የተነሳን ፅዋ እንደየአመጣጡና እንደየጣዕሙ በጋራ ለመጎንጨት እኔ የሚለውን ወደ እኛ የኑሮ ዘይቤና ማንነት ማምጣት ያዋጣል፡፡

3. በፍቅር አይን መተያየት

በተለይ የባለትዳሮችን የህይወት ጓዳ ድረስ የመዝለቅ፣ የትዳርን ሳንካዎች በመካፈል የመቆልመምን ዕድል ለበርካታ ዓመታት ለታደሉት አማካሪዎች የትዳር ህይወት የተለየ ትንታኔ አለው፡፡ የትዳር ህይወት በገሀዱ ዓለም የጓዳ መድረክ የሚከወን የመንትዮች ተውኔት ሌላ ምዕራፍ ሲሆን ከእነዚህ መንትዮች (ባልና ሚስት) የታዳሚነት ድርሻን ብቻ ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቀው የተዋናይም የታዳሚንም ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህ በባለሙያዎቹ አይን ሲታይ የራስንም የተጓዳኝንም የክወና ብቃት በትዳር ህይወት ውስጥ ለመፈተሽና ስለ አንደኛው አጋር ያለ አመለካከት ሁለቱንም ወገን ያስተያየና ያገናዘበ እንዲሆን ይረዳል፡፡
የተጓዳኝ የእርስ በርስ አመለካከት ሳንካን ሲያስከትል የሚያስተውለው በአብዛኛው ወደ ትዳር ከተገባ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ‹‹ከመጋባታችን በፊት የነበረው ያ ሁሉ እንክብካቤ ያ ሁሉ ጉርሻ፤ ያ ሁሉ በሞቴ… ያ ሁሉ ቁልምጫ… ኧረ እጅና ጓንት ነበር የሚሉን… የዛሬን አያደርገውና ክንዶቹ ከቦታቸው ቢታጡ ቢታጡ ቀሪ አድራሻቸው ከወገቤ ነበር…›› የሚል የባለትዳር ሴቶች ስሞታ ከትዳር አማካሪዎቹ ጆሮ በተደጋጋሚ ለመድረስ አለመቦዘኑ እውነታውንና ችግሩን አጉልቶ ያሳያል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ልክ ከሁለቱም ወገን እንዳልታየ የዳኝነት ውጤት ‹‹ያብዬን ወደ እምዬ›› ላለመለጠፍ መጠንቀቅና የተጓዳኝ ድክመቶች (ግድፈቶች) አነጣጥሮ በማየት አቃቂር ከመፈለግ ‹‹በአንተ ትብስ…›› በጥላቻ አይን መተያየቱ ትዳርን ከማናጋት አይመለስም፡፡ በፍቅር አይን መተያየት በራስና በተጓዳኝ ውስጥ ያሉትን የፍቅር ችሮታዎች ትክክለኛ ገፅታ በቅጡና በትኩረት በመመልከት ለግድፈቶች የሚሰጥን ትኩረት በማቅለል እውነተኛ ፍቅርን በእውነተኛ ገፅታው ማቆም ይቻላል፡፡ ስለዚህ በፍቅር አይን በመተያየትና የሚያፈቃቅሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥንዶች እውነተኛን ፍቅር በአይናቸው ለማየት እንደሚችሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡

4. የአመለካከት ልዩነቶችን ከአንድ ውስጥ ማውጣት

በተጓዳኞች ግንኙነት ውስጥ (በተለይ በባለትዳሮች) ሊከሰቱ የሚችሉ በርካታ የአንድነት ልዩነቶች በአመለካከት መለያየት አስታከው ከተፍ ማለታቸው አይቀርም፡፡ ከባለትዳሮች የትዳር ጎጆ እግር የጣለውንና ይህን መሰል ፅዋ እየተጎነጨ የደረሰ ወይም የደረሰበት ሁሉ የልዩነቶቹን ጣዕም በቅጡ ያውቃቸዋል፡፡
አንደኛው ወገን የሌላኛውን አመለካከት ለመቀየርና ለማሳመን የራሱን አመለካከት አክርሮ በመያዝ ‹‹እኔ ያልኩት ብቻ›› የሚልን አቋም ሲያራምድ ይስተዋላል፡፡ በተለይ ወረት ያላየውና እውነተኛን ፍቅር ጋልበው ከትዳሩ ዓለም መግባት ለሚሹት ጎጆን ከመቀለሳቸው አስቀድመው በመካከላቸው አንድነታቸውን የሚወስኑና ሁለትነታቸውን ብቻ የሚያመለክቱ በርካታ የህይወት ፍልስፍናዎች (እውነታዎች) በየግላቸው እንዲያዙ የሚያደርጉ አሉ፡፡
ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የአመለካከት ልዩነቶች ከቀለሱት ጎጆ በር ሲያንኳኩ እንዳመጣጣቸው ለማስተናገድና ለመሸኘት የማይዳግታቸው፡፡ በተጨማሪም ፍቅርና ትዳር የመማማርና በመተራረም ሂደት የሚያሳድጉት እንደሆነ ቀስ በቀስ የሚረዱትና በሙሉ እርግጠኝነትና ተስፋ የዘላቂ የፍቅር ደጀን የሚሆናቸው፡፡

5. ለእውነተኛ ፍቅር አሸናፊነት መጣር

በመፈቃቀር የጥንድነትን ጉልበት መግለጥና የፍቅርን ፍቱን ኃይል መጋበዝ የሚቻለው ከሁለቱም ወገን በተውጣጣ የፍቅር ኃይል ነው፡፡ ጥንዶች ከየግላቸው የሚያዋጡት የፍቅር መስዋዕት (መፈቃቀር) ከአንድ መዋሉ ደግሞ ታላቅ የፍቅር ኃይልን በመፍጠር ለእውነተኛ ፍቅር ዘላለማዊ ጉልበትን ይቸራል፡፡
‹‹ከመቀበል ይልቅ መስጠትን ማስቀደም›› የፍቅር ቀዳሚ መርሆ እንደመሆኑ መጠን ፍቅርን ለመቀበል ፍቅር መስጠትን በማስቀደም ‹‹ከእኔነት›› በቀደመ ይልቁንም በ‹‹እኛነት›› የሚፀናውን እውነተኛ ፍቅር ከእጅ ማስገባቱ አይዳግትም፡፡
በትዳር ዓለም እያሉ ለዚህ ትዳር ዘለቄታ ይነስም ይብዛ ደፋ ቀና ማለት አይቀርም፤ በዚህን ወቅት ፍቅርን መስጠት ማስቀደሙ በፍቅር ህይወት የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በፍቅር ኃይል በመግዛት ለመፍታት ፍቱን ጉልበትን ይሰጣል፡፡
የትዳር ህይወትን በአሸናፊነት ለመወጣት አንደኛ ወገን ሌላውን ለማሸነፍ (ለመግዛት) ከመሽቀዳደም ይልቅ በእውነተኛ ፍቅር (የመፈቃቀር) ጉልበት ለትዳሩ ለመገዛትና ለፍቅር አሸናፊነት ቅድሚያን መስጠቱ ይመረጣል፡፡ በእነዚህና መሰል የፍቅር ሀሳቦች ውስጥ መስዋዕት የሆኑለት ራሱ ፍቅር ነገ እነሱን መልሶ በፍቅር ይጠግናቸውና ፍቅር በፍቅር ያደርጋቸዋል፡፡ የፍቅር ሰዎችም ሆነን እንደ ምሳሌ የምንነሳ ያደርገናል፡፡ ለተጋቢዎችም ለአዲስ ተፈቃቃሪዎችም መልካም ፍቅር ይሁንላችሁ፡፡

ስለዓይንዎ 8 ነገሮችን እንጨዋወት

አይኔ አያትና…
አይኔ ጉድ አደረገኝ፤
አይኗ ጎላ ጎላ…
የሚሉ ብዙ ዘፈኖች ከተዘፈነለትና ከተሞገሰው አይናችን የበለጠ የተሞገሰ የሰውነታችን አካል ያለም አይመስለኝም፡፡

መቼም ዓይናችን የዓለምን ገፅታ በማየት ደስታና እርካታ በውስጣችን እንዲፈጠር የሚረዳን የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡ ሰው ሰራሽ ካሜራ ምስሎችን ለመቅረፅ ካለው ችሎታ በብዙ ሚሊዮን እጥፍ ይበልጥ አይናችን ምስሎችን የመቅረፅ ብቃት አለው፡፡ አይናችንና አዕምሯችን ባላቸው አስደናቂ ግንኙነት በዓለም ላይ ለሚታዩ ብዙ ነገሮች ትርጉም መስጠት እንችላለን፡፡ የአንድን ነገር ርቀት ለመመዘን፣ ቁሶችን በቀላሉ ለማወዳደር፣ ፅሑፎችንና ምስሎችን ለመተርጎም በማስቻል ረገድ ሌላም የአይናችን ሚና ቀላል አይደለም፡፡ እኛም፣ ብዙ ሰዎች ስለ አይናችን በተደጋጋሚ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና ለግንዛቤ ይረዳሉ ብለን ያመንባቸውን ሃሳቦች ከዚህ በታች አቅርበናል፡፡

1

 ሰዎች የተለያየ የዓይን ቀለም ለምን ኖራቸው?

 ሁለት ቡናማ ዓይን ያላቸው ወላጆች ብዙ ጊዜ የሚወልዱት ልጅ ቡናማ የሆነ የዓይን ቀለም ይኖረዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ሰማያዊ የዓይን ቀለም ያላቸው ወላጆች የሚወልዱት ልጅ ሁሌም ለማለት ይቻላል፣ የዓይኑ ቀለም ሰማያዊ ነው፡፡ ነገር ግን የአንዳቸው የዓይን ቀለም ቡናማ ሆኖ የሌላኛው ሰማያዊ ቢሆን፣ የልጃቸው ዓይን በብዛት ቡናማ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ቡናማ የዓይን ቀለም በዘር የመተላለፍ ብቃቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዓለም ላይ ቡናማ ዓይን ያላቸው ሰዎች ቁጥራቸው ሰማያዊ ዓይን ካላቸው በጣም በዝተው የተገኙት፡፡

 

ለዓይናችን ቀለም የሚሰጠው አይሪስ የተባለው የዓይናችን ቀለማማ ክፍል ነው፡፡ የዓይናችንን የቀለም አይነት የሚለየውና የአይሪስ ቀለም የሚሰጠው ደግሞ ለመላው የአካላችን ቀለም በመስጠት የሚታወቀው ሜላኒን የተባለው ኬሚካል ነው፡፡ ከፍተኛ የሜላኒን መጠን ቡናማና ጠቆር ያለ የዓይን ቀለም እንዲኖረን ሲያደርግ፣ ዝቅተኛ የሜላኒን መጠን ደግሞ ሰማያዊ ወይም ፈዛዛ አረንጓዴማ የዓይን ቀለም እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀላ ያለ(ፒንክ) የዓይን ቀለም ያላቸው ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሜላሊን እጥረት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡

 2. ከሁለቱ ዓይኖችዎ ይበልጥ የቱን ይጠቀማሉ?

 ከቀኝና ከግራ እጃችን አንዱን ይበልጥ እንደምንጠቀም ሁሉ፣ አይናችንንም እንዲሁ ከቀኙና ከግራው አንዱን አብልጠን እንጠቀማለን፡፡ ከግራና ከቀኝ ዓይን የበለጠ የሚጠቀሙት በካሜራ በኩል ለማየት ወይም በመርፌ ውስጥ ክር ለመክተት የሚጠቀሙበትን ዓይንዎን ነው፡፡

 የትኛውን ይበልጥ እንደሚጠቀሙበት ለማወቅ ከፈለጉ፣ ይህንን ሙከራ ይሞክሩ፡፡ የአንደኛውን እጅዎትን አውራ ጣትና ሌባ ጣት አገናኝተው ክብ ይስሩ፣ በክቡ በኩል በቤት ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለውን ነገር፣ ለምሳሌ የበሩን እጀታ ይመልከቱ፡፡ በመጀመሪያ አንዱን ዓይን ጨፍነው በሌላኛው በክቡ በኩል ይመልከቱ፡፡ ቀጥለው ደግሞ ሌላኛውን ጨፍነው በክቡ በኩል ያለውን የበሩን እጀታ ይመልከቱ፡፡ ይበልጥ የሚጠቀሙት የበሩን እጀታ በደንብ ማነጣጠርና ማየት በቻለ ዓይንዎት ነው፡፡

3. ብዙ ማንበብ የማየት ችሎታን ይቀንሳል?

 እስካሁን ድረስ ብዙ ማንበብ በዓይን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት መኖሩ አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ለረጅም ሰዓት ቴሌቪዝን መመልከት ወይም በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ መስራት ዓይናችንን እንዲደክም ያደርገዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ብዙ ስራ ስንሰራ ሰውነታችን እንደሚደክም ሁሉ ለረጅም ሰዓት አንድ ነገር ላይ ስናተኩር የዓይናችን ጡንቻዎች ስለሚደክሙ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ዓይናችንን የመድከም ስሜት ከተሰማን በድካም ምክንያት ሳይሆን መነፅር የሚያሳዝዝ የዓይናችን የውስጥ ክፍል ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ የዓይናችን መድከም የዓይን በከፍተኛ ሁኔታ የመጎዳት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ ህክምና ማዕከል ጎራ ብሎ ሁኔታውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

 

ጥሩ ብርሃን ያለበት ቦታ ዓይን እንዳይደክም ይረዳል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ለማንበብ ወይም ለመስራት የሚቀመጥበት ቦታ ብርሃንን ከጎኑ በአንድ በኩል ብቻ በሚያገኝበት ቦታ ማድረግ ይገባል፡፡ በሚሰራው ወይም በሚያነበው ነገር ላይ ጥላ መፍጠር የለበትም፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እናቶች ልጆቻቸው ልከኛ የሚባል ብርሃን በማይገኝበት ቦታ ሲያነቡ እንደሚጨነቁት፣ ብርሃን በጣም በቂ ከሚባለው ባነሰ ቦታ ላይ መስራት ያን ያህል በዓይን ላይ አደገኛ ጉዳት አያስከትልም፡፡

4

 

ዓይን ለምን ደም ይለብሳል?

 

አቧራ፣ ጭስ እና ሌሎች ጥቃቅን ነገሮች በዓይናችን ውስጥ ሲገቡ ዓይናችንን ደም እንዲለብስ ወይም እንዲቀላ ያደርጉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜ፣ ትኩሳት፣ ከተለያዩ የውስጥ ህመሞች የተነሳ ድካምና ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጥ መጠጣት አይናችንን እንዲቀላ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡

 

ብዙ ጊዜ የዓይን መቅላት የተወሰነ የህመም ስሜት ቢፈጥርብንም አስጊ የሆነ ጉዳት ግን አያስከትልብንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዓይናችን የሚቀላበት ምክንያቱ በጀርም ወይም በሌሎች ተህዋሲያን ተጠቅቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ኮንጃክቲቪቲስ የተባለው የዓይንን ቆብ የሴል ሽፋንን የሚያጠቃ በሽታ ዓይናችንን ያቀላዋል፡፡ ስለዚህ ዓይናችን በተደጋጋሚ የሚቀላ ከሆነ የኮንጃክቲቪቲስ  በሽታ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የዓይን ህክምና ወደምናገኝበት ማዕከል ጎራ በማለት ምርመራ ማድረግ ይገባናል፡፡

5. ሜካፕ መጠቀም ዓይንን ይጎዳል?

 በኮስሞቲክስ ውስጥ የሚገኙት ቅመሞች ለአንዳንድ ሰዎች አለርጂክ ይሆንባቸዋል፡፡ በእርግጥ በቆዳቸው ላይ አለርጂክ ለሚፈጠርባቸው ሰዎች ታስበው የተዘጋጁ የተለዩ ኮስሞቲክሶች አሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ኮስሞቲክስ አለርጂክ የሚሆንባቸውና ፈፅሞ ለሜካፕ የማይመቹ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡

 

ብዙዎቹ የዓይን ኮስሞቲክሶች በቀላሉ እንዳይበላሹ የሚያግዝ ንጥረ ነገር ተጨምሮባቸው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ሆኖም ከጊዜ በኋላ ኮሞቲክሶቹ በቆዳችን ላይ ከሚገኙት ባክቴሪያዎች ጋር ንክኪ ፈጥረው በመዋቢያ መሳሪያው ላይ ሊያርፉ ይችላሉ፡፡ የመዋቢያ መሳሪያው በሌላ ቀን በሜካፑ ብልቃጥ ላይ ሲያርፍ ባክቴሪያዎቹ በብልቃጡ ውስጥ ገብተው ቀስ በቀስ መባዛት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ የዓይን ሜካፕ የሚጠቀሙ ሰዎች የሚጠቀሙትን ሜካፕም ቶሎ ቶሎ በመቀየር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

 

የዓይንን ሜካፕ ሆነ መዋቢያ መሳሪያውን ፈፅሞ ለሌላ ሰው ማዋስ አይገባም፡፡ በኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቆች ውስጥ የሜካፖችን አይነት ለማሳየት ለናሙናነት የተቀመጡ ኮስሞቲክሶችን ከመሞከርም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

 

አንድን ሜካፕ ሲጠቀሙ ዓይንዎት ላይ የማበጥ ወይም የማሳከክ ስሜት ከተፈጠረብዎት ወዲውኑ ሜካፑን መጠቀም ያቁሙ፡፡ ማቆም ብቻ ሳይሆን ሲጠቀሙበት የነበረውን ሜካፕና መቀቢያ መሳሪያውን የቆሻሻ ገንዳ ውስጥ መጣል ይገባዎታል፡፡ ፎጣና መታጠቢያ ጨርቆች በባክቴሪያ ሊበከሉ ስለሚችሉ የቤተሰብዎ አባላት በእጃቸው እንዳይነኩት ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሜካፕ አጠቃቀምን ከዓይንዎን ጤንነትና ከውበት ምርጫዎ በማነፃፀር ሊጠቀሙ ይገባል፡፡

6

 

ዓይንን ሆን ብሎ ማጠናገር ጉዳት ያስከትላል?

 ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው አይናቸውን ሲያጠናግሩ በዚያው ተጠናግተው ይቀራሉ ብለው ይሰጋሉ፡፡ ነገር ግን የአንድ ሰው የዓይኑ ጡንቻዎች ዓይኑን በሚገባ ግጥም አድርገው ለመያዝ ብቁ የሚሆኑበት በሶስት ዓመቱ ነው፡፡ ስለዚህ ልጆች ለጨዋታ ወይም የወላጆቻቸውን አትኩሮ ለማግኘት ብለው የፈለጉትን ያህል በተደጋጋሚ ዓይናቸውን ቢያጠናግሩም ዓይናቸው ተጠናግሮ አይቀርም፡፡

7

 

ዓይንዎ የፍቅር መግቢያ ሲሆን

 

‹‹ፍቅር እንደ እንባ ነው፤ ከዓይን ይመነጭና ልብ ላይ ያርፋል›› ነበር ያለው  ሶቢያን ሶሪስ የተባለ አንድ ምሁር፡፡ እውነትም የፍቅር መቀመጫው ልብ ላይ ነው ቢባልም መግቢያው ዓይን ነው፡፡

 

ለነገሩ ብዙ ነገሮቻችን በመግቢና በመውጪያ አካላቶቻችን ይገለፁ እንጂ የነገሮቻችን ሁሉ መገለጫ ምንጭ አንጎላችን ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት በፍቅር ለመማረክ አንድ ሰው የማረከውን ወይም የማረካትን ወደ ራሳቸው ለማምጣት የሚያነሳሳቸው ነገር መጀመሪያ የሚያዩት በዓይናቸው እስከሆነ ድረስ ለመመሰጣቸው መነሻ የሆናቸው ዓይናቸው ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለየትኛውም እይታችን መልስ የሚሰጠንና ለእይታችን (ለመማረካችንም ሆነ ለመመሰጣችን) ምላሽ የሚሰጠን አንጎላችን ነው ማለት ነው፡፡ ያው ዓይናችን ግን ትልቁን ሚና የሚጫወትልን ይሆናል ማለት ነው፡፡ መቼም ‹‹ዓይኔ አያትና አይኔ ወደዳት… ለምን አይን አየ ተብሎ ዓይን አይከሰስም›› እንዳለው ዘፋኙ ዓይናችንን ከማየት መከልከል አንችልምና እናያለን፤ እንመሰጣለን፤ እንማረካለን፤ ከተሳካ እንፈቃቀራለን፡፡ ታዲያ አይናችንን የፍቅር መግቢያ ብንለው ትክክል አያሰኘንም ትላላችሁ፡፡

8

 

የዓይን ሽፋንና የዓይን ውበት

 

በተለያየ ወቅት ሰዎች ከሰውነታቸው ክፍል እንደሌሎቹ አካላቸው ዓይንንም ለይተው በማውጣት የዓይንን ውበት ሲያደንቁ ይሰማሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ዓይን ጎላ ጎላ ሲል የተለየ የዓይን ውበት እንዳላቸው አድርገው ይቆጠራል፡፡ ዓይን ሰፋ ያለውን አካባቢ እንደመያዙ ጎላ ጎላ ብሎ ሲታይ ለፊትም ሆነ ፊት ላይ ላሉ ሌሎች የፊት አካላትም ውበትን ያላብሳል፡፡

 

ሌላው በዓይን ሽፋን በተለይም የታችኛው ቆዳ ላይ ሜላኒን ከሚባለው ኬሚካል በቦታው በዝቶ ከመገኘት የተነሳ ጠርዙ ተለይቶ ጥቁር የሚሆንባቸው ሰዎች አሉ፡፡ ይህ መጥቆር የህመም ምልክትም ሊሆን ስለሚችል መለየት ይገባል፡፡ ጤናማ በሆነ መልኩ ከተገኘ ግን ለዓይን የበለጠ ውበትን የማጎናፀፍ ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ በተለይ ሴቶች የታችኛውን የዓይናቸውን የሽፋን ቆዳ በኩል ወይም በሻዶ ሲያጠቁሩ የምናየው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ታዲያ ዓይንም መጥፎ ጥላቻን ለመግለፅ እንጠቀምበታለን፡፡ ለምሳሌ ዓይንህን ላፈር…፣ አይኔ እንዳያይህ/እንዳያይሽ እያልን እንገልፃለን፡፡ ይህ ታዲያ የዓይንን ብዙ ቋንቋ የሚናገር አይመስላችሁም? መቼም ውበትም ቋንቋም እንደተመልካቹና እንደተናጋሪው ሰው ነው ቢባልም የዓይን ውበትና መገለጫ ቋንቋዎቹ ግን የጋራ የሆነና አብዛኛውን ሰው የሚያስማሙ ናቸው፡፡

ልጆች በአጋጣሚ ከወደቅን ወይም አፋችን ሲመታ አንዱ  ወይም ብዙ ጥርሶች ሊጎዱ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ በአከባቢያችን ወደሚገኝ  የጥርስ ክሊኒክ ወይም የህክምና ተቋም መሄድ አለብን። ልጆች ጥርሳችን አዲስ የእድገት ደረጃን የሚያመላክት ስለሆነ ጥርስ የመፋቅና ተስማሚ ምግብ የመመገብ ጥሩ ባህሪይ ማካበት አስፈላጊ ነው ።

ጥርስን መጠበቅ
የታችኛው መንጋጋ ትንንሽ ጥርሶች እንደተለመደው መጀመሪያ ይወጣሉ። ይሄም የሚከሰተው  ከስድስት እስከ ስምንት ወራት እስኪሆነን ነው። ነገር ግን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው ሊወጡ ይችላሉ። ከዚያ ቀጥለው የሚወጡት የላይኛው መንጋጋ የፊት ጥርሶች ሲሆኑ በመከተልም የፊት ጥርሶች፣ ክራንቻ እና በመጨረሻም የኋላኞቹ የመንጋጋ ጥርሶች ይወጣሉ። በአብዛኛው ልጆች እድሜያቸው ከሁለት ተኩል እስከ ሶስት አመት ሲሆናቸው ሁሉንም የወተት ጥርሶች ማለትም አስር ከላይ አስር ከታች ያበቅላሉ።

የጥርስ መቦርቦር
ስኳር ለጥርስ መቦርቦር ምክኒያቱ ነው። ልጆች ስኳር አዘል የሆነ ምግብ ስንበላ ወይም ስንጠጣ በአፍ ውስጥ ያለው ባክቴሪ አሲድ በማመንጨት ጥርስ እንዲበሮቦር ያደርጋል።  ስለዚህም ከመመገቢያ ሰአት ውጪ ስኳር የያዘ ነገር ያለመብላት ወይም ያለመጠጣት ጥሩ ነው።

ጥርሳችንን ማፅዳት
ከጫወታ ወደ ቁም ነገር ፤ የመጀመሪያ ጥርስ በትንሽ እና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ማፅዳት ይችላል። ጥርስ መቦረሹን እንደ ጨዋታ መጀመር ይቻላል። ጥርሳችንን በቀን ሁለት ጊዜ በጥርስ ሳሙና መፋቅ አለብን፡

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1381#sthash.asqI99de.dpuf

ከደባሪ ህይወት እና ስሜት ተላቆ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር የሚያስችሉ 6 ጥበቦች

Posted by tenadam on July 15, 2014 // 1 Comment

·          

·          

·          

·         8067

 

EmailShare

6
ያለፈውን ነገር እንደገና መመለስ እንደማትችል እወቅና ተቀበል

በተገቢው ጊዜ ተገቢ ስራ ባለመስራትህ ተሳስተሃል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ሀዘንህን ግለፅ፡፡ ‹‹ወይኔ›› ብለህ አልቅስና ይውጣልህ፡፡ ይህ ያለፈውን ስህተት ለመቅበር ይረዳሃል፡፡ ስላለፈው ህይወትህ ስታስብ በየጊዜው ሐዘን፣ ድብርትና ተስፋቢስነት እንዳይሰማህ ያግዝሃል፡፡

5
ነገ በአንተ አዲስ ቀን መሆኑን እመን

38 ዓመት ምናልባት በከንቱ አልፏል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ለአንተ የህይወትህ መጨረሻ አይደለም፡፡ የአማካይ ሰው ዕድሜ ብንወስድ እንኳ ገና ብዙ ዓመታት አሉህ (56-38)፡፡ ስለዚህ ለውጥ በማምጣት በአዲስ የህይወት ጎዳና ላይ መራመድ ትችላለህ፡፡ አሁን በመጣልህ ማስተዋል ተጠቅመህ የዛሬውን/የነገውን ሕይወትህን መለወጥ እንደምትችል እመን፡፡

ትኩረትህ በትናንት ላይ ሳይሆን በነገ ላይ ይሁን፡፡ ያለፈውን የህይወት ዘመንህን ቆርጠህ መጣል አትችልም፤ የህይወትህ ታሪክ ነው፡፡ ሆኖም አቅጣጫህን ወደ ኋላ ሳይሆን ወደ ፊት ማድረግ ትችላለህ፡፡ በአዕምሮህ ነገን/ወደፊትን ከተመለከትህ ትናንት ከአንተ ኋላ ይሆናል፤ በአዕምሮህ ትናንትን የምትመለከት ከሆነ ደግሞ ፊትህ ወደ ትናንት ጀርባህ ደግሞ ወደ ነገ ይሆናል፡፡ አንተ ትናንትን በማሰብ ሳይሆን ነገን በማሰብ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህ፡፡ በትናንትህ ውስጥ የሚታጨድ መልካም ነገር የለም፤ በነገ ውስጥ ግን ደስታን ሊያመጣ የሚችል ተስፋ አለ፡፡ ትናንት ጨለማ ነው፤ በነገ ውስጥ ግን የህይወት ብርሃን ተስፋ ይኖራል፡፡ ስለዚህ ‹‹ከእኔ ትናንት ይልቅ የእኔ ነገ ተስፋ አለው›› የሚል እይታ ይኑርህ!

4
ተስፋ ሳትቆጥ አዎንታዊ እርምጃ ውሰድ

ከዚህ ከሚደብርህ ህይወት ለመላቀቅ አይነተኛው መንገድ የአንተ ለለውጥ ለመስራት ያለህ ቁርጠኝነት ነው፡፡ የምትፈልገው ግብ (የግል ደህና ገቢ ያለውን ስራ መያዝ) ሩቅ ሊመስልህ ይችላል፤ በእርግጥ ሊሆንም ይችላል፡፡ ሆኖም በርትተህ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ከወሰድክ በረጅም ርቀት ያሰብከው ቦታ ትደርሳለህ፡፡ ከዚህ በላይ በየዕለቱ የምትወስዳቸው መልካም እርምጃዎች እያስደሰቱህ ይመጣሉ፡፡ ሌላው ደግሞ የግል ደህና ገቢ ያለው ስራ መሆኑን እንጂ ስራው ምን አይነት እንደሆነ፣ ይህን ስራ ለመስራት አሁን በእጅህ ያለው ግብአት (ዕውቀት፣ ገንዘብ፣ ምቹ ሁኔታዎች ወዘተ) መለየት እንዲሁም ከግብ የሚያደርስን ተጨባጭ ስልት ማውጣት ጠቃሚ ነው፡፡ ተገባራዊ እርምጃ ካልወሰድክ ግን መልካም ሐሳብህን በክፉ ሐሳብ ገደልከው ማለት ነው፡፡ ‹‹የአንድ ሺ ኪሎ ሜትር መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀምራል›› የሚባለውን አባባል ሰምተህ ይሆናል፡፡ በቀሪው ህይወትህ ጠንክረህ በትጋት ከሰራህ ለውጥ ታመጣለህ፤ ካልሆነ ግን ይህም ጊዜ እንደ ወጣትነቱ ጊዜ ምንም ስራ ሳይሰራበት ያልፍና እውነተኛ ጨርቅ ጥሎ መብረር ሊከሰት ይችላል፡፡

3
አዎንታዊ እይታን አጎልብት

አሁን ያለው አስታሰብህ/እይታህ አሉታዊ ይመስላል፡፡ ‹‹ይህ ነው የሚባለው ምንም ዋጋ ያለው ነገር በህይወቴ እንደሰራሁ አይሰማኝም›› የሚለው ሀሳብ አሉታዊ ነው፡፡ ከአንተ ተጨባጭ እውነታ አንፃር ይህ እውነታ ቢሆንም፣ በህይወትህ መልካምና ጠንካራ ነገሮችም ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ያለውን ነባራዊ እውነታ መቀበል አንድ ነገር ሆኖ በአሉታዊ እይታ መሞላት ግን የተለየ ነው፡፡ ‹‹እኔ ዜሮ ነኝ›› የሚለው ሐሳብ ራስን ወደ መኮነን፣ ከዚያም ወደ ድብርት/የመንፈስ መውደቅ፣ ሲበዛ ደግሞ ራስንም ለማጥፋት ወደማሰብ ሊያመራ ስለሚችል አዕምሮህን ከአሉታዊ አስተሳሰብ ለመጠበቅ ሞክር፡፡ ለምሳሌ አንተ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ዲፕሎማ አለህ፤ ከሰዎች ጋር ደግሞ ተግባቢ ትመስላለህ (ጨዋታ አዋቂ አይነት ነኝ ብለሃል)፣ አሁን የዕለት ተዕለት ወጪህን የሚሸፍን የገቢ ምንጭ አለህ… ስለዚህ ባዶ አይደለህም፡፡

2
ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርህን ተው

በተለይ የአንተ ጓደኞች በወጣትነታቸው ጊዜ ተገቢውን ስራ በመስራታቸው አሁን መልካም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንተ አሁን በቀሪው ዘመንህ የቻልከውን ያህል በመሮጥ አሁን ካለህበት ወደ ፊት ፈቀቅ ማለቱ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የሚያዋጣህ ከዚህ በኋላ የምትሰራቸውንና ውጤቱን ቀድሞ ከነበረህ ህይወት ጋር ማነፃፀር እንጂ ከሌሎች ሰዎች ጋር ራስህን ማወዳደር ራስህን አሳንሰህ እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡

1
ፍቅርና ትዳርን ማሰብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል

የትዳርም ሆነ የፍቅር አጋር እንደሌለህ ተናግረሃል፡፡ ይህ በምርጫ/በውሳኔ ነው ወይስ ባለመሳካቱ ነው? አሁን የቀድሞ ጓደኞችህ ከአንተ ጋር የሉም፤ ወላጆችህም እስከ መጨረሻ ከአንተ ጋር አይኖሩም፡፡ (አሁን በህይወት ካሉ) ስለዚህ የኑሮ አጋር መፈለግ በኑሮም ሆነ በስሜት ለመደገፍ ጥቅም አለው፡፡

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ።

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1939#sthash.adbv6GLh.dpuf

የስራ ማጣትና የገቢ አለመኖር ህይወቴን አጨለመው፤ ምን ይሻለኛል?

Posted by tenadam on June 5, 2014 // Leave Your Comment

·          

·          

·          

·         740

 

EmailShare


የ25 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ በ2004 መጨረሻ ከአለማያ ዩኒቨርሲቲ በፕላንት ሳይንስ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቄያለሁ፡፡ ስመረቅ ብዙ ተስፋ እና ራዕይ ነበረኝ፣ ነገር ግን ስራ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ተመልሶ የቤተሰብ ጥገኛ መሆን ለጭንቀት ዳርጎኛል፡፡ ስንት ሲጠብቁብኝ ተመልሼ ቤተሰቦቼን ሳስቸግር እነሱንም እያሳዘንኩ ነው፡፡ በርካታ ቦታዎች ባመለከትም አንዳንዱ አይጠራኝም ከተጠራሁም ደግሞ ገና በአንደኛ ዙር ያሰናብቱኛል፡፡ በውጤት እንዳልል ጥሩ የሚባል ውጤት አለኝ፤ ነገር ግን በቃ እንደ ዕድል ሆኖብኝ ጓደኞቼ ሁሉ ባለ ስራ ሆነው እኔ ከሰው በታች መሆኔ እያናደደኝ ራሴን ለጫት እና ለመጠጥ ሱስ ሰጥቻለሁ፡፡ ከቤተሰብም ሆነ ከማውቃቸው ሰዎች ጋር መስማማት አልቻልኩም፡፡ በትንሽ ነገር እናደዳለሁ፡፡ እቆጣለሁ፡፡ እጣላለሁ፡፡ አሁን አሁን እንደውም ‹‹ስራ አገኛለሁ›› የሚለው ሀሳብ ከውስጤ ስለጠፋ መፈለግም ትቼያለሁ፡፡ በህይወት መኖርም ትርጉም እያጣሁበት መጥቻለሁ ካለ ምንም ስራ ወጥቼ ወደ ቤት ስመለስ በራሴ አዝናለሁ፡፡ በአጠቃላይ የማደርገው ነገር ጠፍቶኛል፡፡ ስለዚህ እናንተ መላ አታጡም እና እስቲ መላ በሉኝ፣ ማድረግ ያለብኝን ነገር ጠቁሙኝ ችግሬ አፋጣኝ ነው እና አፋጣኝ መልሳችሁን አድርሱኝ፡፡
አሌክስ ከልደታ

መልስ፡- ሃይ! አሌክስ እንደምን ሰንብተሃል፡፡ ያደረስከንን ሰላምታም ሆነ አድናቆት በክብር አመስግነን ተቀብለናል፡፡ ደንብኝነትህም ተጠናክሮ ይቀጥል ለማለት እንፈልጋለን፡፡ ውድ ጠያቂያችን ካደረስከን ደብዳቤ ላይ እንደተመለከትነው በጥሩ ውጤት በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ከዓመት በፊት የተመረቅክ ቢሆንም እስካሁን ስራ አለማግኘት ለጭንቀት እና ለተስፋ መቁረጥ እንደዳረገህ እና በሱስ እንድትጠመድ እንዲሁም የተናጋ ማህበራዊም ሆነ ቤተሰባዊ ህይወት እንዲኖርህ እያደረገህ እንደሆነ ተገንዝበናል ምን ማድረግ እንዳለብህም መፍትሄ እንድንጠቁምህ ጠይቀሃል፡፡

የተከበርከው ጠያቂያችን በቀጥታ ወደ መልሱ ስንገባ በመጀመሪያ ደረጃ ለተወሰነ ጊዜ ስራ ማጣት እና መፍታት በርካታ አዳዲስ ተመራቂዎች ከሚገጥማቸው ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ አንተም የዚህ ችግር ተጠቂ በመሆንህ ያን ያህል በህይወትህ ተስፋ እስከ መቁረጥ የሚያደርስ የስሜት መረበሽ ውስጥ መግባት የለብህም፡፡ ሁልጊዜ ደግሞ ስለማጣትና ስለ መቸገር ማሰብ የለብንም፡፡ አንተም ውስጥህን በመጀመሪያ ሞልተኸው፣ ስራ አገኛለሁ ብለህ አስብ /Abundance mentality/፡፡ በርካታ አዳዲስ ተመራቂዎች ተመርቀው እንደወጡ ስራ ያገኛሉ በርካታዎቹ ደግሞ በተቃራኒው ረዘም ላለ ጊዜ ስራ ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ ይህ ጊዜ ደግሞ ጭንቀታቸውንም ከፍ ያደርገዋል፡፡ አንተም ላይ የሚታየው የዚሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ እኛም አንተን እንደ ባለሙያ የምንመክርህም ሆነ የስነ ልቦና ሳይንስም የሚለው በመጀመሪያ ደረጃ አንተ የተማርክ ነህ፡፡ ስለዚህ በቀዳሚነት ስለመቀጠር ሳይሆን ስራን ስለ መፍጠር ነው ማሰብ ያለብህ፡፡

ነገር ግን ስራ ለማግኘት ማወቅ ያለብህ እና መተግበር ያለብህ መርህ አለ፡፡ እሱም ስራ የሚገኘው የማስታወቂያ ቦርድን በማንበብ፣ የጋዜጦችን የክፍት የስራ ቦታ ገፆችን በማገላበጥ ብቻ አይደለም ይልቁኑ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑ ስራዎች የሚገኙት ከእነዚህ የመረጃ ምንጮች ውጭ ባለ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሲባል በተለይ በርካታ የግለሰብ ድርጅቶች በጋዜጣ ወይንም ቦርድ ላይ ሳይወጡ ሰራተኛ የመቅጠር ልማድ ያላቸው፡፡ ይህ ደግሞ የሚፈጠረው ጠንካራ የሆነ የእርስ በእርስ ግንኙነትን በመፍጠር ነው፡፡ ስለዚህ አንተም ስራ እየፈለግክ መሆንህን ለሚያውቁህ እና ለምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ ንገር፡፡ ስራ አገኘህ ወይ ብለው ሲጠይቁህ ከማፈር እና ከመሸማቀቅ ይልቅ እንዳላገኘህ እና እንደምትፈልግ በግልፅ የመናገር ድፍረት ይኑርህ፡፡ ስራ እየፈለክ መሆንህን ለጓደኞችህ፣ ለቅርብም ሆነ ለሩቅ ዘመዶችህ ንገር በአጋጣሚ የሰሙት ክፍት የስራ ቦታ ካለ ይጠቁሙሃል፡፡ ይሉንተኛ አትሁን… ከአንተ ሙያ ጋር ግንኙነት ያላቸው እና ሊቀጥሩኝ ይችላሉ ብለህ የምታስባቸው ድርጅቶችን አነጋግር፣ የምትውልበትም ቦታ አንተን ወደ ስራ የሚወስድ እና ምርታማ የሚያደርግህ ቦታ እንጂ ለሱስ የሚያጋልጥና ወደ ኋላም የሚጎትትህ ቦታ መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ አሁን እየዋልክበት ያለኸው ቦታ አንተን የሚጠቅም እና የምትፈልገው ቦታ እንድትደርስ የሚረዳ አለመሆኑን ተገንዘብ፡፡

ውድ ጠያቂያችን ጀማሪ ሠራተኞች ወይንም አዲስ የሆኑ ተመራቂዎች ሊያደርጉት ከማይገባ ነገር መካከል የመጀመሪያው ‹‹ሰራ አለማምረጥ ነው›› ስለዚህ አንተም ስራ ማማረጥ የለብህም የተገኘው ቦታ ላይ በተገኘው ደመወዝ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሁለት አይነት ጥቅም አለው፡፡ የመጀመሪያው የስራ ልምድ እንድትይዝ ያደርግሃል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተረጋጋ ህይወት እንድትመራ እና በተረጋጋ መንፈስ የተሻለ ነገር እንድትፈልግ ያደርግሃል፡፡ የተገኘውን ነገር ሳይዙ በባዶ እጅ ሌላ የተሻለ ነገር መመኘት የማይቻል ነገር ነው፡፡ በትምህርት ጥሩ ውጤት መያዝ ለብቻው ስራ እንድናገኝ ሊያደርገን እንደሚችል አስብ ተገቢ ሲቪ ማዘጋጀትም አስፈላጊ ነው፡፡ በርካታ አዳዲስ ተመራቂዎች የሲቪን ጥቅም አይረዱትም ነገር ግን ሲቪ ማዘጋጀትም አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቪ ማለት እኛ በሌለንበት እኛን የሚወክል ስለ እኛ የሚመሰክር ነው፡፡ ስለሆነም በደንብ መዘጋጀት ይኖርበታል፤ ሲዘጋ የአንተን የስራ፤ የትምህርት እንዲሁም የህይወት ታሪክ በዝርዝር እንዲያሳይ ሆኖ መዘጋጀት ይኖርበታል፤ ይህም ሲባል የሰራሃቸው ስራዎች የተሳተፍክባቸው ስልጠናዎች ካሉ በዝርዝር ከነቀኑ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡ የትምህርት ደረጃ፣ ያለህ ፍላጎት፣ ራዕይ፣ ክህሎት እና ለድርጅቱ ልትሰጥ የምትችለው ጥቅም በዝርዝር ማሳየት ይገባል፡፡ እንግዲህ ሲቪ በእኛ የስራ መፈለግ እና ማግኘት ወሳኝ የሆነ ሚናን የሚጫወት መሆኑን ከተገነዘብክ ሲቪ ስናዘጋጅ ማድረግ ያለብንን ነገሮችንም እንመልከት፡፡ እንግዲህ ሲቪ ከአራት እና አምስት ገፅ መብለጥ የለበትም፣ ምንም አይነት የሐሰት ማስረጃን መጠቀም የለብህም፡፡ በመጨረሻም ስም እና አድራሻ በአግባቡ መስፈሩን ማጣራት ያስፈልጋል፡፡

እንግዲህ ይህ ነገር በአግባቡ ከተዘጋጀ በኋላ ነው፡፡ እንግዲህ አንተ ሊቀጥሩኝ ይችላሉ ብለህ የምታስባቸው ድርጅቶች ጋር በግንባር ሄደህ አናግር፣ በጋዜጣ እና በቦርድ ላይ የወጣ ስራ ብቻ አትጠብቅ፣ በቅርብ ያሉ ሰዎችም እንዲተባበሩህ አድርግ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች ላይ የመሰማራት ልማድ ይኑርህ ይህም ሲባል ካለ ክፍያ ስራ እየሰራህ የስራ ልምድ የምታገኝበትን ሁኔታ መፍጠር ወይንም ተግባራዊ የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ ራስህን ወደ ስራው ለማስገባት ትችላለህ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቃለ መጠይቅ ወቅት በአግባቡ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ መዘጋጀቱ ደግሞ የቃለ መጠይቅን ምንነት ከመገንዘብ ይጀምራል፡፡ እንግዲህ አንድ ድርጅት አንተ ለድርጅት ከሌላው ተወዳዳሪ በተለየ መልኩ ልታቀርብና ልታበረክት የምትችለው አስተዋፅኦን ማወቅ ፈልጓል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ለቃለ መጠይቅ ከመሄድህ በፊት ምን ልጠይቅ እችላለሁ ብለህ አስብ፡፡ ስለ ድርጅቱ የስራ ዘርፍ አስፈላጊ ስለሆኑ እውቀቶች፣ ‹‹ክህሎቶች ዝርዝር ነገር እወቅ፣ በተቻለህ መጠንም ድርጅቶች ውስጥ የሚሰራ እና ስለ ድርጅቶች እና ስለ ስራው ባህሪ ከሚያውቅ ሰው ጋር መነጋገር በቂ የሆነ መረጃ እንዲኖርህ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻም ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ከገባህ በኋላ ንቁ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ንቁ መሆን ደግሞ ማለት እኛ ካሰብነው ጥያቄዎች ውጭ ጥያቄዎች ሊመጡ እንደሚችሉ ማሰብ እና መዘጋጀት ማለት ሲሆን ቀድመው ደግሞ የሚጠይቁህ ችግሮችን የመፍታት ችሎታህን /Problem Solving Skill/ ሲሆን በስራ ወቅት የተለያዩ ችግሮች ቢገጥሙህ በምን መልኩ ትቆጣጠራቸዋለህ የሚለው ጥያቄም ሆነ ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን ተረጋግቶ የመመለስ ልማድ ይኑርህ፡፡ በራስ የመተማመን መንፈስ በደንብ ሊታይብህ ይገባል፣ አትደነባበር መረበሽ እና መደናገጥ ደግሞም የሚመጣው አይሳካልኝ ይሆን፣ እወድቅ ይሆን በሚሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችና ጥርጣሬዎች የተነሳ ስለሆነ ይህንን አይነት አሉታዊ የሆነ አስተሳሰብ አስወግድ ካልሆነ ግን የአንተ መረበሽ እና መደነጋገር በቀጣሪዎችህ ላይ የሚፈጠረው ምስል የተሳሳተ ሊሆን ስለሚችል በችሎታህ እና በብቃትህ እንዲጠራጠሩህ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦችህ ላይ ተጠንቀቅ አይሳካም ብለህ ስራ ለመወዳደር አትሄድ፡፡

እንግዲህ እነዚህ ነገሮች በአግባቡ ከተገበርክ ሌላው ነገር ደግሞ አለባበስ ነው እንደ ስነ ልቦና ሳይንስ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለሚፈጠር ጠንካራም ሆነ ደካማ ማህበራዊ ግንኙነት መሰረቱ በሰዎች ላይ እኛ በመጀመሪያ በምንፈጥረው ስሜት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ስራ ለመወዳደር ስትሄድ በቀጣሪዎችህ ላይ ጥሩ ስሜት መፍጠር መቻል አለብህ ይህን አይነት ስሜት ደግሞ መፍጠር የምትችለው በጥሩ በመናገር እና ጥሩ የሆነ አለባበስ እንዲሁም ጠንካራ የሆነ በራስ የመተማመን መንፈስን በማሳየት ነው፡፡ አነጋገር ሲባል በተጠየክበት ነገር ዙሪያ ሙያዊ የሆነ እና ከአንተ ደረጃ የሚጠበቅ ስራ መስራት ሲሆን አለባበስ ጋር ግን ስንመጣ ቀጣሪዎች ላይ ጥሩ ስሜት የመፍጠር ችሎታ እና ብቃት ሊኖረን ይገባል፡፡ አለባበስን በተመለከተ አንድ ስምምነት ባይኖርም ጥሩ ሳቢነት ያለው እና ቦግ ያላለ ሱፍ ከተመሳሳዩ ወይም ከተዛማጁ ሸሚዝ ካስፈለገም ጋር ማድረግ የሰው ቀልብ በመሳብ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ በራስ የመተማመን መንፈስንም በተመለከተ ደግሞ ጥሩ በራስ የመተማመን መንፈስ ካለን በቀጣሪዎችን ዘንድ ግርምትን እና መደነቅን እንዲሁም መፈለግን ያስከትላል፡፡

የተከበርከው ጠያቂያችን አንተ እኮ ግራ ልትጋባ አይገባህም፡፡ ምክንያቱም ተምረሃል የራስህን የሆነ ነገር ስለመፍጠር ይህን ያህል እኮ ብታስብ አንድ ነገር ላይ መድረስ ትችላለህ፡፡ ደግሞ በቤት ውስጥ በመቀመጥ እኮ የሚገኝ ነገር የለም፡፡ ከሰዎች ጋር መነጋገር፣ መመካከር ያስፈልጋል፡፡ ከቤተሰብም ጋርም ሆነ ከጓደኞችህ ጋር መጋጨት ደግሞ ምን አመጣሁ? ምንስ ይጠቅማል? አንተንም ይረብሻል ጤናማ ያልሆነ ማህበራዊ ግንኙነት ደግሞ የስነ አዕምሮ ቀውስ የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ግንኙነት የመፍጠር ችሎታ ይኑርህ፤ የተረጋጋ እና ጥሩ ሰብዕና ሲኖርህ በሰዎች ዘንድ ክብርን ተቀባይነትን ማግኘት ትችላለህ፡፡ በአጠቃላይ ግን ስራ መፈለግ የራስ የሆነ የስነ ምግባር መርህ አለው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያው ጥሩ የሆነ የእርስ በእርስ ግንኙነት መፍጠር መቻል ነው፡፡ ጥሩ የእርስ በርስ ግንኙነት የሚፈጠረው ደግሞ ጤናማ የሆነ ሰብዕናን በመላበስ ነው፣ ጥሩ ሰብዕና ያለው ሰው ደግሞ ተስፋ አይቆርጥም፣ የሚያደርገውን ያውቃል፣ ጥሩ የሆነ የማህበራዊ ግንኙነትም ባለቤት ነው፡፡ ስለዚህ አንተም የዚህ አይነት ሰብዕና ባለቤት ልትሆን ይገባል፡፡

ውድ ጠያቂያችን ቀደም ሲል እንደጠቀስነው አንተ ላይ እየታየ ያለው የስሜት መረበሽ በርካታ ስራ አጥ ሰዎች ላይ የሚስተዋል የስሜት መረበሽ ነው፡፡ እኛ ግን እንደ ባለሙያ የምንለው ነገር አንተ ወጣት እንደመሆንህ መጠን ስራን ከመጠበቅ ይልቅ ወደ መፍጠሩ ብትገባ እስከዛም ሌሎች የተለያዩ የስራ ማግኛም አቅጣጫዎችን ብትመለከታቸው የተሻለ ውጤታማ መሆን ትችላለህ፡፡ በህይወትህ ግን ‹‹ጨለምተኛ መሆን›› የለብህም፡፡ እራስህን ለመለወጥ ማዘጋጀትም አስፈላጊ ነው፡፡

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1845#sthash.QYVD6A3h.dpuf

ላፈቀርካት ሴት ያለህን የፍቅር ስሜት እንዴት መግለፅ ትችላለህ?

Posted by tenadam on November 20, 2013 // 18 Comments

·          

·          

·          

·         455

 

EmailShare

ከቅድስት አባተ
ፍቅርም ሆነ መፈቃቀር ለሰው ልጆች በሙሉ ያለመድልዎ የተሰጠ ፀጋ ነው፡፡ ፍቅር የሁላችንም አካል ነው፡፡ በፍቅር የተሞላና የተሻለ የፍቅር ኑሮ እንዲኖረንም የብዙዎቻችን ምኞት ነው፡፡ ታዲያ የእኛው ሆኖ ሳለ ብዙዎቻችን ፍቅርን አንቀበለውም ወይም እናባርረዋለን፡፡ ፍቅርንመ ሰጥተን እንዳንቀበል ብዙዎቻችን ማዕቀብ የተደረገብን ይመስለናል፡፡ ፈላጊና ተፈላጊ ሳይገጣጠሙ ሲቀሩ ደግሞ ፍቅር እንደተራብን ልንቆይ ግድ ይለናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የፍቅር ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚገደዱት ወንዶች በመሆናቸው ይህን የፍቅር ስሜት ለመግለፅ በህይወታቸው ውስጥ ትልቁ የቤት ስራ ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን የፍቅር ስሜታችንን ለመግለፅ የሚኖረን አካሄድ ከልጅነት አስተዳደጋችን ጋር ተያይዞ የሚመጣና ውስጣችን ተቀርፆ ባለው መልኩ ለፍቅር በደረስንበት ዕድሜ ላይም እንደ ችግር ወይም በተቃራኒው እንደ ጥሩ ነገር ልናንፀባርቀው እንችላለን፡፡
ለዚህም ነው አስቀድመን ፍቅር የሚለውን ቃል ራሱ ስናስብ በአዕምሯችን ሀሳባዊ የሆነ ነገር እንስላለን፡፡ እዘህ ላይ ልናይ የሚገባን ነገር ልጆች እያለን ምንም የምንስለው ሀሳባዊ ነገር በፍቅር ዙሪያ ስላልተነገረን ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ብቻ ከዕድገት ለውጣችን ጋር በሚፈጠረው ፍቅር ልባችንን ክፍት አድርገን እንቀበላለን፤ ለማጣጣምም እንሞክራለን፡፡ በሀሳባዊ ስዕል ውስጥ በቅፅበት የሳልነውን ፍቅር ለማግኘት ደግሞ ስለሚከብደን እየተፈቀርን እንኳን ፍቅርን እንራባለን ወይም እያፈቀርን እንኳን የተፈቃሪን ልብ ማግኘት ያስቸግረንና ፍቅርን እንራባለን፤ ያለመገጣጠም ማለት ይህ ነው፡፡ እንደ ልጅነታችን ቢሆን ኖሮ እኮ ሰዎች ትኩረት ስለሰጡን ወይንም ልናገኘውና የእኛ ልናደርገው የምንፈልገውን ነገር አንድ ሰው ሲያደርግልን የፍቅር ስሜቱ በቀላሉ ይገባና ተፈቀርን ብለን እናስብና የፍቅር ረሃባችንን እናስወግድ ነበር፡፡ ያ ማለት ትኩረት የሰጠን ወይንም የምንፈልገውን ነገር የሰጠን ሁሉ አፍቃሪያችን እንደሆነ እናስብ ነበር ማለት ነው፡፡ ታዲያ አድገን የእኛ እንዲሆን የምንፈልገው ፍቅር እንደ ልጅነታችን ከብዙዎች መምጣቱን ሳይሆን እኛው ካፈቀርነው ሰው ብቻ ምላሹን መጠበቃችን ሁለቱን የተለያዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ለማፍቀር በደረስንበት ዕድሜ ወቅት አፍቅሮ እንዲፈቀሩ መፈለግ ወይም ለፍቅር መጠያየቅ ተፈጥሯዊ እንደሆነ ማወቅ የግድ የሚሆነው፡፡ እንደ ተፈጥሮነቱ ፍቅርን ስንፈልግ ደግሞ የህይወት አጋርን የመፈለግ ጉዞ ውስጥ እንገባለን፡፡ በዚህ የመፈላለግ ጉዞ ውስጥ ታዲያ የሁለቱም ተፈላላጊዎች መገጣጠም ይኖርና ነገሩ ቀላል ሊሆንላቸው ይችላል፡፡ ለአንዳንዶቹ ደግሞ ፈላጊው ራሱ አፍቃሪ ይሆንና ተፈቃሪዋ ብዙም መፈቀሯን ሳታውቅ በፍለጋ ብቻ ረዥም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይህ በተለይ ወንዶች ላይ በብዛት የሚንፀባረቅ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ምክንያት ደግሞ በብዙ ልማዶችና እምነቶች የፍቅር ጥያቄን ማቅረብ ያለበት ወንድ ነው የሚል እሳቤ ሰርጾ ስለነበር ነው፡፡ ይህ አመለካከት በተወሰነ መልኩ የተቀየረ ቢሆንም በብዛት ግን አሁንም ሴቷ እያፈቀረችውም ቢሆን የፍቅር ጥያቄው ከወንዱ እንዲመጣ የመፈለግ ዝንባሌ አለ፡፡ ይህን ሁኔታ ወንዶች አቅልለውት በመመልከት ፍቅራቸው የሚበልጥባቸው ከሆነ ፍርሃታቸውን አስወግደው የፍቅር ጥያቄያቸውን አስወግደው የፍቅር ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ከተሳካላቸው እኮ ከሴቷ የበለጠ የአሸናፊነት ስሜት የሚሰማቸው ወንዶቹ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ረዥሙን ሂደት የተጓዙትና ድል ያደረጉት እነሱ ናቸውና፡፡ ታዲያ ወንዱ ከራሱ የፍቅር ስሜት በመነሳትና ውስጡን በማዳመጥ ይጀመርና ማንነቷን ከለየ በኋላ እንዴት ፍቅሩን ሊገልፅላት እንደሚችል ማወቅ አለበት፡፡
ገና ስታያት ልብህ የደነገጠላትን ሴት እንደምንም ብለህ ማናገር አለብህ፡፡ በደንብ ለመግባባት እንድትችሉ ደግሞ በተቻለህ አቅም መንገድ ላይ እየሄዳችሁ ከሆነ የተገናኛችሁት መንገድህን ቀይረህ ከእሷ ጋር በመሄድ ጨዋታችሁን አራዝም፣ በታክሲም ውስጥ ከሆነም እንዲሁ መንገድህን አሳልፈህ በመሄድ በተቻለህ አቅም በደንብ ለመግባባት የሚያስችላችሁን ረዘም ያለ ወሬ በማውራት ተጨዋወቱ፡፡ ስትለያዩም ሌላ ጊዜ እንድትገናኙ ስልክ ቁጥሯን ተቀበላት፡፡ አንድ ሶስት ቀን በስልክ ከተገናኛችሁ በኋላ አንድ የእረፍት ቀን ተገናኝታችሁ ሻይ ቡና እንድትሉ ጠይቃት፡፡ በመቀጠልም የምትገናኙበትን እያንዳንዷን ቀን ከፋፍላቸውና ማንነቷን በደንብ የምታውቅበት አንተም ማንነቷን የምትገልፅበት የፍቅርንም ስሜት የምትረዳበት አድርጋቸው፡፡ እነዚህን በግንኙነታችሁ ተከታታይ ቀናት ምን እንደሚመስሉ እናያቸዋለን፡፡
1. የመጀመሪያ ቀን ግንኙነት
የመጀመሪያ ቀን ስትገናኙ ስለ ስራዋ፣ በስራ ቦታና ስላጋጠማት ነገር፣ ስለ ቤተሰቦቿ እናም ከፍቅር ውጭ ስለሆኑ ሌሎች ጉዳዮች አንስታችሁ ተወያዩ፡፡ በመጀመሪያ ግንኙነታችሁ ከፍቅር ውጭ በተለመዱ ጉዳዮች ላይ መነጋገራችሁ ሳትጨናነቁ ዘና ብላችሁ እንድታወሩ ይረዳችኋል፡፡ ስታወሩ ታዲያ በደረቁ ሳይሆን የተለያዩ ቀልዶችን እያነሳህላት አስቃት፡፡ በጨዋታ የታበ ቆይታችሁ ደስ የሚል ጊዜን እንድታሳልፉ ከማድረጉም በላይ አንተ የማታጨናንቅ ቀለል ያልክ ሰው እንደሆንክ ስለምትረዳ እሷም ነፃነቷን ያገኘች ያህል እንዲሰማትና እንድትጫወት ታደርጋታለህ፡፡ እዘህ ጋር መጠንቀቅ ያለብህ ነገር ከእሷ የበለጠ ብዙ አታውራ፣ ለእሷ ሰፊውን ጊዜ ስጣትና አንተ ብዙውን ጊዜ አድማጭ ሆነህ ተገኝ፡፡ የሚያዳምጣትን ሰው በማግኘቷ በጣም ደስ ይላታል፤ ለአንተም ቦታና ክብር ትሰጥሃለች፡፡ ይህን ማድረጋችሁ ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን እሷም ካንተ ጋር በድጋሚ ተገናኝታ የምታወጉበትን ቀጣይ ቀን እንድትናፍቅር ያደርጋታል፡፡ ስለ ቀጣይ የመገናኛ ቀናችሁም ትንሽ ተባባሉ፡፡ ነገር ግን የግድ በዚህ ቀን ካልሆነ ብላችሁ አትወስኑ፡፡ መደዋወል እንደምትችሉ ተማምናችሁ ተለያዩ፡፡ ስትለያዩ ቢቻል እስከተወሰነ መንገድ ዎክ እያደረጋችሁ ብትሄዱ ወይም ቤቷ ልትደርስ ግማሽ መንገድ እስኪቀራት ድረስ አብራችሁ በታክሲም ብትሄዱ፤ ያለበለዚያ በትራንስፖርት አሳፍረሃት ብትመለስ የመሳሰሉትን እንደ አማራጭና እንደ ሁኔታዎች እያየክ መፈፀም ከቻልክ አንድ ትልቅ ማህተም መተህ እንደላካት ልትቆጥር ይገባሃል፡፡
2. የሁለተኛ ጊዜ ግንኙነት
በስልክ ጥሩ የሆኑ አስደሳች ንግግሮችን ካደረጋችሁ በኋላ ብዙም ሳትርቁ ለሁለተኛ ጊዜ የምትገናኙበትን ቀን ተነጋግራችሁ ተቀጣጠሩ፡፡ ታዲያ ለሁለተኛ ጊዜ ለመገናኘት ስትቀጥራት እንደመጀመሪያ ጊዜያችሁ አነስ ያለ ቦታ ወይም ካፌም ሳይሆን ሬስቶራንት ቢሆን የምትጋብዛትም ሻይ ቡና ሳይሆን ምሳ ወይም እራት መሆን አለበት፡፡ ስትገናኙ አለባበሷንና ስብዕናዋን ሁሉ አድንቅላት፡፡ ታዲያ አንተም የራስህን ስብዕና የሚጠብቁ አለባበስና አቀራረብ ይዘህ ተገኝ፡፡ ጋባዡ አነተ ብትሆንም የምትፈልገውን ነገር እንድታዝ ነፃነቷን ስጣት፣ ካላወቀችውም አሪፉን ነገር አስረዳትና የተሻለውን እንድትመርጥ አድርጋት፡፡ በዚህ ቀን የሚኖራችሁን ሰፊ ሰዓት ስለግል ሕይወታችሁ በስፋት በማውራት እየተጨዋወታችሁ አሳልፉ፡፡ በግንኙነታችሁ መቀራረብ ውስጥ ውስጧንም እያጠናህ መሄድህን እንዳትረሳ፡፡ የበላችሁት የጠጣችሁት ነገር እንደተመቻት ጠይቃት ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልግ ከሆነም እንድታዝ አድርግ፡፡ የሁለተኛ ቀን ውሎዎቹ በጥሩ ሁኔታ ከተጠናቀቁ በድጋሚ ሌላ ቀን ለመገናኘት እንደምትቀጣጠሩ አሳውቃት፡፡ የምትቀጣጠሩ ቀን ግን ከተለያያችሁበት ጊዜ በጣም የረዘም መሆነ የለበትም፡፡ ያሳለፋችሁት ጣፋጭ የሆኑ ጊዜያቶች ከአዕምሯችሁ ብዙም ሳይጠፋ ሳትርቁ ለመገናኘት ሞክሩ፡፡ ታዲያ ቀጠሯችሁ ከተሳካ አሁንም በሬስቶራንት ውስጥ መሆኑን ተነጋገሩ፡፡ ወጪ ለመቀነስ ብለህ ወደኋላ ተመልሰህ ካፌ ውስጥ ወይም የወረደ ቦታ ለመቀጣጠር አትሞክር፡፡ ከእንግዲህ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ የሚያስብልህ ምንም ነገር የለም፡፡ የዚህን ቀን ውሏችሁን አጠናቃችሁ ከመለያየታችሁ በፊት ወንድ እንደመሆንህ ነገሮች ከአንተ አፍ ቅድሚያ ይጠበቃሉና በቆይታችሁ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍህን ንገራት፡፡ እሷን በማግኘትህና አንተን አክብራ ከአንተ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሆና በመገኘቷ በጣም ደስ እንዳለህም አሳውቃት፡፡ እሷን ሁሌ ብታገኛት እንኳን እንደምትደሰት ንገራትና ቶሎ ቶሎ እንደምትደውልላት በመግለፅ ለወደፊቱ ስሜትህን በቀላሉ ለመግለፅ እንዲያመችህ ዳር ዳር ማለት ትጀምራለህ፡፡ እንደተለመደው ከሸኘሃት በኋላ በንጋታው ደውልላት ትናንተ በጣምጥሩ ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ንገራት የእሷንም ስሜት ጠይቃትና ቀጣዩ ስራህን ፍቅር ፍቅር እያሰኘህ ለማስኬድ ልታስብበት ተዘጋጅ፡፡
3. የሶስተኛ ቀን ግንኙነት
በዚህ ጊዜ ዕድለኛ ከሆንክ ራሷ ደውላ ባለፈው ጥሩ ጊዜ እንዳሳለፈች ገልፃልህ በድጋ እንድትገናኙ ትጠይቅሃለች፡፡ ይህን ካደረገች ጥልቅ የሆነ ስሜት በውስጧ እንደተፈጠረባት ያሳያል፡፡ ለአንተም የምትመችህ አይነት ሴት መሆኗን ካረጋገጥክ የፍቅር ጥያቄውን ማቅረብ ቀላል ሊሆንልህ ይችላል፡፡ በዚህ ወቅት ምንም ነገር አላለችም ማለት ግን ምንም ስሜት የላትም ማለት አይደለም፡፡ አሁንም ስሜቷን ለመግለፅ ተቆጥባ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ስልክ ደውለህ ካነጋገርካት በኋላ ስሜቷን ስላልገለፀች መክፋትህን ሳታስነቃ ሌላ ቀን እንደምትደውልልለት ነግረህ ተሰነባበታት፡፡ በተቻለ አቅም ለሶስተኛ ጊዜ እንድትገናኙ እንደምትፈልግ ራሷ እስክምትገልፅልህ ድስ ስልክ እየደወልክ ብቻ ጠብቅ፡፡ ነገር ግን ስሜቷን እንድትገልፅ ፈፅሞ መገፋፋት የለብህም፡፡ ምክንያቱም ከተነቃብህ ውስጧ ቶሎሊረበሽ ይችላልና እንዳማረህ ይቀራል እንጂ ትንፍሽ አትልልህም፡፡ ከዚህም አልፎ ይህ የችኩልነት ባህሪ ሊያስጠላት ይችላል፡፡ ሶስተኛው ቀን በጣም ወሳኝ እንደሆነ አስብና በስልክ ደስ የሚሉ ወደ ፍቅር የሚያመሩ ወሬዎችን በቀልድ መልክ አውራት፡፡ በሞባይልም ከሆነ ደስ የሚሉ ፍቅርን ሊጠቁሙ የሚችሉ ነገር ግን በጣም ፍቅርን በግልፅ የሚያሳዩ ሆነው ያላፈጠጡ መልዕክቶችን (SMS) ላክለት፡፡
የእሷ መልስ ላይ ብዙ ትኩረት አታድርግ ወይም አትጠባበቅ፡፡ የሶስተኛው ቀን ግንኙነታችሁ በስልክ ረዥም ሰዓትን የወሰደ ከሆነ ከላይ በተገለፀው መልኩ ነገሮችን ግለፅላት፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ጠብቀህ ካልሳካልህ በቀጣይ ቀናት ራስህ እንድትገናኙ ትቀጥራትና በሌላ ጊዜ ደግሞ እሷ እንድትቀጥርህ እድል ስጣት፡፡ በዚህ ቀን ስትገናኙ ግን ሆን ብለህ ወሬያችሁ ሁሉ በፍቅር ዙሪያ ብቻ እንዲሆን በማድረግ ያላትን ስሜት ለማወቅ ሞክር፡፡ ላንተ የፍቅር ስሜት እንዳላት ከሁኔታዋ ለማወቅ ከቻልክ አንተም ያለህን ስሜት ዳር ዳር እያልክ ግለፅላትት፡ ለምሳሌ ከሰውነቷ ክፍል ፀጉርሽ ወይም ጥርስሽ ያምራል እያልክ፣ የፊትሽ ቆዳ ደግሞ እንዴት ይለሰልሳል እያልክ እየነካካሃት ግለፅላት፡፡ ስሜቷ ግልፅ ካልሆነልህ ግን በቀጥታ በጣም የፍቅር ሰው እንደሆነችና አንተም እንደወደድካት በመግለፅ ያላትን ስሜት እንድትነግርህ ጠይቅ፡፡ ምላሹ እሷም እንደምታፈቅርህ ከገለፀች ፍለጋህ ተሳክቷል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በቀጥታ ደስ የሚል የፍቅር ሽሚያ ውስጥ የሚያስገባችሁን መንገድ ልትከተሉ ትችላላችሁ፡፡ ለምላሿ ጊዜ የምትፈልግ ከሆነም ጊዜ ስጣት ምላሿ ግን ከአንተ ጋር በፍቅር መቆየት እንደማትፈልግ ወይም ሌላ በፍቅር የምትወደው ጓደኛ ካላትና ለእሱ የምትሰጠውን ፍቅር ለአንተ መስጠት የማትችል ከሆነ በዚሁ የፍቅር ፍለጋህን ልታቆም ይገባል፡፡ ከዚህ በላይ እርግጠና ያልሆንከውን ነገር ይዘህ በመጓዝ ጊዜህን ማባከንም ሆነ ከማትሆንህ ሴት ጋር በመኳተን ጭንቀት ውስጥ በመግባት ህይወትህን ከምታበላሽ በጊዜው መፍትሄ ስጠው፡፡ አንተንም የምትብቅ ለአንተ የታሰበችና የተቀመተች ሌላ ሴት ልትኖር ትችላለችና ይህቺ ሴት እየጠበቀችህ ነውና እሷን ብዙ ማስቆም የለብህም፡፡ የሕይወትህን አቅጣጫ ቀይረውና ሌላ ሙከራ ውስጥ ግባ!

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1486#sthash.DZB1TndM.dpuf

 

 

ድንቅ የስነ ልቦና ታክቲኮች: ኃያላንን ለመማረክ ኃያልነትህን ደብቅ (Don’t outshine your master)

Posted by tenadam on May 30, 2014 // 1 Comment

·          

·          

·          

·         1411

 

EmailShare

ከሊሊ ሞገስ

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ታትሞ የወጣ)

በማንኛውም የስራ መስክ ስኬታማ ለመሆን ከሰዎች ጋር ተግባብቶ አብሮ የመስራት ብቃት ሊኖረን ይገባል፡፡ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና የፈለጉትን ለማግኘት ደግሞ የሰዎችን ባህሪና ፍላጎት ቀድሞ የመገንዘብ ችሎታ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የሰዎችን ባህሪ ለመገንዘብ የዓመታት ጥረት እና ልምምድን ይጠይቃል፡፡ ጥረት እና ልምምዱን የምናደርገው እንዲሁ በደመ ነፍስ ሳይሆን የሰዎችን ስነ ልቦና በማጥናት ነው፡፡ የሰዎችን ስነ ልቦና በማየት ወይም አብሮ በመሆን በቀላሉ የምንገነዘበው ቀላል ነገር ሳይሆን ጥበብን፣ የረጅም ዓመት ጥናትና፣ ምርምርን የሚጠይቅ ውስብስብና ድብቅ ነገር ነው፡፡

እንግዲህ እርስዎም የሰዎችን ባህሪ ለመረዳት እና ሰዎችን እንደባህሪያቸው ለመያዝ ከፈለጉ ይህንን ሁሉ መንገድ ማቋረጥ አለቦት፡፡ ወይም ደግሞ ሰዎችን መረዳት የሚችሉበት አቋራጭ መንገድ መፈለግ፡፡ ምን ጊዜም ረጅሙን መንገድ ከመጓዝ አቋራጩን መንገድ መጠቀም እደሚያፈጥን የታወቀ ነው፡፡ የሰዎችን ባህሪና ማንነት ለመረዳት የሚያስችሎት አቋራጩ መንገድ ረጅምን መንገድ የተጓዙ ሰዎች ያቀረቡትን መረጃ፣ ሀሳብ እና መርህ መዳሰስ ነው፡፡
ለዛሬ ከሰው ልጅ ባህሪ ውስጥ ብዙዎችን የተጠናወተውን የኃያልነት ስሜት እንዴት መቋቋም እንዳለብን እና ኃያል የሚባሉ ሰዎችን ምን አይነት ብልጠት ተጠቅመን ከእነሱ የፈለግነውን ነገር ማግኘት እና ያሰብነውን ነገር ማሳካት እንድንችል የሚረዳንን የመጀመሪያውን መርህ እናቀርብሎታለን፡፡
ሁሉም ሰው ኃያልነትን ይፈልጋል፡፡ ደካማ መሆንንም ሆነ መምሰልን ማንም አይፈልግም፡፡ በሰዎች ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም ወይም ኃይል የሌለን መስሎ ሲሰማን ሁላችንም ስሜታችን ይጎዳል፡፡ ሆኖም ግን በዘመናችን በየትኛውም የዓለም ክፍል ኃያል ለመሆን ያለንን ፍላጎት እና የኃይል ጥማታችንን በሚያሳብቅ መንገድ ካንፀባረቅን አደገኛ ችግር ሊያጋጥመን ይችላል፡፡

በዚህም የተነሳ ምን ጊዜም ቅን ባንሆንም ቅን መሆን በሚገባን ስፍራ ቅን መስለን መታየት፣ ኃያል መሆን የምንፈልግ ቢሆንም ኃያል ሆኖ መታየታችን የሚጠላና የሚያስጠቃን ከሆነ ደካማ ሆነን መቅረብ ይገባናል፡፡
በዘመናችን በየሀገሩ ሲነገሩ የምንሰማቸው አያሌ መፈክሮችና መርህዎች ተጨባጭ የሆነውን እውነታ የተቃረኑ ናቸው፡፡ ‹‹ዓለም በልጽጋለች፣ ዘመን ተለውጧል፣ በዚህ በበለፀገ ዘመን የሀገር መሪዎች ፍትሃዊ፣ ለዴሞክራሲ ተገዥና የህዝብን የበላይነት የተቀበሉ መሆን አለባቸው፡፡ ማንኛውም ሰው ምንም ሆነ ምንም እኩል መብት አለው›› የሚሉና መሰል መርህዎችና መፈክሮች በብዛት ሲደሰኮሩ ይደመጣል፡፡

እርሶ በቅንነት እነዚህን ለመሳሰሉ አባባሎችና መርሆዎች በሙሉ ሳያወላውሉ ከተከተሉ እና ለመርህዎች ተገዥ ከሆኑ ሁልጊዜ በዙሪያዎት ያሉ እንደ እርሶ ሞኝ ያልሆኑ ብልጣብልጦች ወደ ታች ይጫንዎታል፡፡ ሁሉንም ሰው በስራው፣ በእውቀቱ በችሎታው የላቀውንም እውቀት የሌለውንም በተመሳሳይ መንገድ ማስተናገድ ማለት በሰዎች መሀከል ያለውን ልዩነት አለመገንዘብ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ምንም ችሎታ የሌላቸውን ደካማ ሰዎች ከሚገባው በላይ መካብ፣ ጠንካራ እና ብርቱ የሆኑትን ደግሞ እንደ ማንኳሰስ ይቆጠራል፡፡ ሰዎችን እንደ እውቀታቸው፣ ችሎታቸው እና ስራቸው ልዩነት ፈጥሮ መመዘንና መንከባከብ ደግሞ ለድካማቸውና ለስራቸው ዋጋ እንደመስጠትና እንደማበረታታት ይቆጠራል፡፡

ኃያል ሰዎችን መቆጣጠሪያ መርህ

‹‹ምን ጊዜም ከእርሶ በላይ ኃያል የሆኑ ሰዎች የኃያልነት ስሜት እንዲሰማቸው ያድርጉ፡፡ የእንዲህ አይነት ሰዎችን ቀልብ ለመማረክ ወይም በእነሱ ዘንድ ለመደነቅ ችሎታዎትንና ብቃትዎን አጉልተው አያውጡ፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ነገር በተቃራኒው በእነኚህ ሰዎች ላይ ፍርሃት ሊያሳድር ስለሚችል ሊጠሉ እና ለብቀላ ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከእርስዎ በላይ የሆኑ ሰዎችን በመማረክ ኃያል ለመሆን ከፈለጉ እነዚያ ሰዎች ካላቸው ኃያል በላይ ኃያል መሆንዎን በጥበብ ይግለፁ፡፡

ከዚህ መርህ በተቃራኒው መንገድ ከተጓዙ ግን በህይወትዎ ላይ አስከፊ ጉዳት ለሚያስከትልቦት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ በአንድ ወቅት የፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስቴር የነበረው ኒኮላስ ፎኩዌት ይህንን መርህ በመጣሱ የገጠመውን እናካፍልዎት፡፡

ፎኩዌት ሉዊስ አስራ አራተኛ የፈረንሳይ ንጉስ ሆኖ ሲመረጥ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሆን ተሰየመ፡፡ በዚህ ስራው ባገለገለበት የመጀመሪው ዓመት በጣም ለጋሽ፣ ድል ያለ ግብዣ ማዘጋጀት እና ውብ ሴቶችን የሚወድ እና መምራት ለሚፈልገው የቅንጦት ህይወት ገንዘብና ስልጣን ፈላጊ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በስራው ትጉህ እና በንጉሱም ዘንድ ተቃሚ ሰው ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ በ1661 የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረው ዳላስ ማዝሪን ሲሞት ፎኩዌት እሱን ቦታ ንጉሱ እንደሚሰጠው ተማምኖ ነበር፡፡ ንጉሱ ግን የጠቅላይ ሚኒስቴርነት የስልጣን ቦታ እንዲቀር አደረገ፡፡ ፎኩዌት ንጉሱ ይህን ያደረገው ለእሱ የነበረው ክብርና ግምት ስለቀነሰ ስለመሰለው አስደናቂ ነገር የመስራት ችሎታውን ሊያሳየው ወሰነ፡፡

በነጋታው ስራውን የጀመረበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ድል ያለ ፓርቲ አዘጋጀ፡፡ ፓርቲው በዚህ ሰበብ ቢዘጋጅም ዋነኛ አላማው ግን ተጋባዥ እና ታላቅ እንግዳ ለነበሩት ለንጉሱ ግብር እንዲሰባሰብላቸው ለማድረግ ነበር፡፡ በግብዣው ላይ በሀገሪቱ ታዋቂ እና በጣም ተወዳጅ የነበሩ ገጣሚያን ተጋብዘው ቀረቡ፡፡ ፓርቲው በሰባት ደረጃ በተመደበ የእራት ስነ ስርዓት ተጀመረ፡፡ በግብዣው ላይ በፈረንሳይ ተወዳጅ ከሚባሉት ምግቦችና መጠጦች ውስጥ የቀረ አልነበረም፡፡ በፈረንሳይ ውስጥ ከዚያ በፊት ተቀምሰው የማይታወቁ አዳዲስ ምግቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅተው ነበር፡፡ ፎኩዌት ለንጉስ ክብር የመረጠው የክላሲካል ሙዚቃ ምግቡን ለማወራረድ በሚመች መልኩ ከክላሲካል ሙዚቃ ተጫዋች ተቀነቀነ፡፡

ፓርቲውን የታደሙት ሹማምንቶችና መኳንንቶች ዝግጅቱ ግሩም እንደሆነ ሲያወሩና ፎኩዌትን ሲያደንቁ አመሹ፣ ምሽቱ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡

በነጋታው ፎኩዌት በንጉሱ ትዕዛዝ ዘብጥያ ወረደ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ የሀገርን ገንዘብ ያለ አግባብ በማባከንና በመዝረፍ ተከሰሰ፡፡ (በእውነቱ ብዙውን ገንዘብ ከንጉሱ ጋር ተነጋግሮ እና ንጉሱ ፈቅዶለት አብረው የዘረፉት ነበር) ፎኩዌት ጥፋተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቀሪውን የ20 ዓመት ዕድሜውን በፈረንሳይ በተራራ ላይ ተገልላ በምትገኘው እስር ቤት እንዲያሳልፍ ተፈረደበት፡፡

የፈረንሳይ ንጉስ የነበረው ሉዊስ አስራ አራተኛ ሲበዛ ኩሩ እና ትእቢተኛ ስለነበር ሁል ጊዜ በዙሪያው ያሉ ሰዎች አትኩሮት እና ክብር ለእሱ ብቻ መስጠት እንዳለባቸው ያምን ነበር፡፡ ፎኩዌት ፓርቲውን ያዘጋጀው ለንጉሱ ያለውን ታማኝነትና ክብር እንዲሁም ጉብዝናውን፣ ታታሪነቱን፣ በሌሎች ዘንድ ያለውን ክብር በማንፀባረቅ ለጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲታጭ በማሰብ ነበር፡፡

ሉዊስ ግን ፓርቲውን የተካፈሉ መኳንትና ሹማምንቶች ፎኩዌትን ሲያሞግሱና ሲያደንቁት ሲመለከት ጓደኞቹ ከእሱ ይበልጥ የበታቹ የሆነውን የገንዘብ ሚኒስቴሩን ሲያወድሱ፣ ፎኩዌትም የንጉሱን ኃያልነት ማሳየትና ንጉሱን ማላቅ ሲገባው ራሱን በማላቁ ተንገበገበ፡፡ በእርግጥ ንጉስ ሉዊስ መንገብገቡን ለማንም አልተናገረም፡፡ የውስጡን በውስጡ ይዞ ደህንነት እንዳይሰማው ያደረገውን ሰው ሰበብ ፈልጎ ከአቅራቢያው አራቀው፡፡ ከዚህ በኋላ ጂን ባብቴዝ የተባለውን አማካሪ በመቅጠር ከፎኩዌት የበለጠ ስሙን ሊያገንለት የሚችል አስገራሚና አስደናቂ ቤተመንግስት አስገነባ፡፡ ቤተ መንግስቱን ሲያስመርቅ የፎኩዌት የህዝብን ገንዘብ ያለ አግባብ በመበዝበዝ በሚል ሰበብ ህይወቱን እንዲከፍል ካደረገው ፓርቲ የበለጠ ገንዘብ የፈሰሰበት ትልቅ ፓርቲ አዘጋጀ፡፡

ታሪኩ እንደሚያስረዳን ልክ እንደ ሉዊስ ሁሉም ሰው ኃያልነት እነጠቃለሁ የሚለው ስጋት ያስጨንቀዋል፡፡ እርስዎም ራስዎ በጥበበኛ ሆልሆኑ ችሎታዎና ሰብራዎ እውቅናን ቢያገኙ እውቅና ማግኘቶን ተከትሎ መከፋት፣ መጨነቅ፣ ጥላቻ እና ደህንነት የማጣት ስሜት ይፈጠርቦታል፡፡
ስለዚህ እንዲህ አይነት ባህሪ እውቅና እና ዝና ባላቸው ሰዎች ላይ በጠቅላላ እንደሚኖር መጠበቅ አለቦት፡፡ በእርግጥ ከእርሶ በላይ የሆኑ ሰዎችን ላለማስከፋት ከመጠን በላይ መጨነቅና መጠበብ አይገባዎትም፡፡ ነገር ግን ከበላዮት ካሉ ሰዎች ጋር በሚፈጥሩት ግንኙነት የተለየ አቀራረብ መከታተል አለቦት፡፡ ብቃትዎንና ችሎታዎን ለፈለጉት ሰው ማሳወቅ ይችላሉ፡፡

ከበላይዎት ባለስልጣን ለሆነ ሰው ወይም ለአለቃዎት ችሎታዎን ለማሳየት መሞከር ግን በጣም ትልቅ ስህተት ነው፡፡

ምናልባት ዘመን ተሻሽሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደ ሉዊስ አይነት አመለካከት ያለው ሰው የለም ብለው ያስቡ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ዘመን የስልጣን እርከን የጨበጡና ዝነኛ የሆኑ ሰዎች አስተሳሰባቸው ልክ እንደ ጥንት ንጉስ እና ንግስቶች ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች የያዙትን ስልጣንና ዝና እንዳይነጠቁ ዋስትና ይፈልጋሉ፡፡ በዙሪያቸው ካሉ ይበልጥ አትኩሮትን የሚስቡ፣ የሚሞከሹ እና የሚወደሱ መሆን እንዳለባቸው ያምናሉ፡፡

ብዙ ሰዎች ለአለቆቻቸው ወይም ከበላያቸው ላሉ ባለስልጣናት የስራ ብቃታቸውን፣ ተሰጥኦዋቸውን እና ተወዳጅነታቸውን በማሳየት ከበላያቸው ባሉ ሰዎች አድናቆትንና ተወዳጅነትን ለማትረፍ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ ብቃትዎንና ችሎታዎን ለአለቃዎት ሲያሳዩት ያደነቆት መስሎ ሊቀርብ ይችላል፡፡ የመጀመሪያ እርምጃው የሚሆነው ግን ልክ እንደ ሉዊስ እርስዎን ከእሱ ያነሰ እውቀት፣ ተሰጥኦና ችሎታ ባለው ሰው መተካት ነው፡፡ ልክ እንደ ሉዊስም እውነታውን ደብቆ እርሶን ያስወገደበትን ሰበብ ይፈጥራል፡፡

‹‹ብቃትዎንና ችሎታዎን ከበላይዎት ላሉ ሰዎች አያሳዩ›› የሚለው መርህ ሁለት ነገሮችን ያስገነዝቦታል፡፡ አንደኛ ራስዎን ሆነው በመቅረብ ብቻ በተዘዋዋሪ ለአለቃዎም ሆነ ከበላይዎት ላሉ ባለስልጣን ችሎታዎን ማሳየት እንደሚችሉ ነው፡፡ ሁለተኛ ከበላይዎት ያለው ባለስልጣን ወይም አለቃዎት ቢወዶት እንኳ የፈለጉትን ነገር መስራት እንደማይችሉ እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ሂዲዮሽ ለተባለው የጃፓን ንጉስ አማካሪ የነበረውና ሊኪ የተባለ ሰው ላይ የደረሰ አደጋ ነው፡፡

ሊኪ በቤተመንግስት ውስጥ የግሉ መኖሪያ ህንፃ የነበረው፣ በንጉሱ እና በህዝቡ ዘንድ የሚወደድ ሰው ነበር፡፡ በ1591 ባልታወቀ ምክንያት ንጉሱ እስር ቤት እንዲገባና ወዲያውኑ በሞት እንዲቀጣ ወሰነበት፡፡ ኋላ ላይ ምክንያቱ ሲጣራ በቀድሞ ጊዜ የተራ ገበሬ ልጅ የነበረው ሊኪ ቤተመንግስት ከገባ በኋላ በገዛ ፈቃዱ ሳንዳልስ የተባለውን የንጉሳዊ ቤተሰብ መለያ አጠለቀ፡፡ ይህ በንጉሱ ሊኪ ወሰን የሌለው መሆኑን አሳየው፡፡

ሊኪ ያን ያደረገው ተወዳጅነትና ስልጣኑን ሊያገኝ የቻለው በራሱ ጥረትና ልፋት ስለመሰለውና ያለበት ደረጃ በንጉሱ እንደሚወሰን ስለሚዘነጋ ነው፡፡ ራሱን በጣም ከፍ ከፍ አድርጎ በመመልከቱ ላጠፋው ጥፋት ህይወቱን እንዲከፍል ተደረገ፡፡

እንግዲህ እርስዎም ከበላይዎት ላሉ ባለስልጣናት ችሎታዎን ማንፀባረቅ የሚያስከትልቦትን ጉዳት በመረዳትና በተቃራኒው መንገድ በመጓዝ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡ ለምሳሌ ከአለቃዎት የበለጠ አዋቂ እና አስተዋይ ከሆኑ ተቃራኒውን ሆነው ይቅረቡ፡፡ አለቃዎት ከእርስዎ የሚበልጥ እንዲመስለው ያድርጉ፡፡
- ለወደፊትም ሆነ በአሁኑ ወቅት ብዙም የማይጎዳዎትን ስህተት ሰርተው አለቃዎት እንዲተባበሮት ይጠይቁት፡፡ ብዙዎቹ ራሳቸውን አግዝፈው የሚመለከቱ ሰዎች እንዲህ ያለውን ትብብር ማድረግ የበላይነታቸውን ስለሚያረጋግጥላቸው ያስደስታቸዋል፡፡

- ከአለቃዎ የተሻለ ጥሩ ሀሳብ ካሎት ለአለቃዎ ነግረው እንዲጠቀምበት ያድርጉ፡፡ የእርሶ ምክር ምንጩና ስር መሰረቱ የእርስዎ ምክር እንደሆነ ያሳውቁት፡፡

- በተፈጥሮዎት ከሰው ጋር ተግባቢና ተጫዋች ከሆኑ አለቃዎትን ወይም ከእርሶ የበላይ የሆነውን ባለስልጣን ከጨዋታ ውጭ እንዳያደርጉት ይጠንቀቁ፡፡ አለቃዎት ልክ እንደ ንጉስ ሉዊስ የሁሉንም አትኩሮት በእሱ ላይ እንዲሆን እንደሚፈልግ አይዘንጉ፡፡ ከሰዎች ዘንድ ያሎትን ተወዳጅነት ወይም የመግባባት ችሎታዎን ለአለቃዎ ለማሳየት መጣር እንደ ፎኩዌት ችግር እንደሚያስከትልቦት ይገንዘቡ፡፡

- ችሎታዎንና ብቃትዎን መደበቅ ደካማ መሆን ሊመስልዎ ይችላል፡፡ ነገር ግን ደካማ መስሎ መታየት ለፈለጉት ስልጣን የሚያበቃዎ ከሆነ ድክመት ሳይሆን ጥንካሬ ነው፡፡

ከበላይዎት ያሉ ሰዎች ኃያልነታቸውን እንዲያንፀባርቁ በመፍቀድ የደህንነት ስሜት በማጣት እርስዎ ሊቃጡቦት ከነበረው አደጋ ይጠበቃሉ፡፡ አለቃዎን ሊገለብጡት የሚችሉት አይነት ከሆነ ግን ችሎታዎን በማሳየት እንደሚበልጡት ያሳውቁት፡፡ ያገኙበትን ችግር በማስፋትም ውድቀቱን ያፋጥኑ፡፡ አለቃዎ በጣም ደካማና ሊወድቅ የደረሰ ከሆነ ግን በራሱ ጊዜ እስኪወድቅ ይታገሱ፡፡

ከበላይዎ ያለውን ሰው ስልጣኑን ሊነቀንቁት የማይችሉት አይነት ከሆነ ግን ከእርሱ እንደሚበልጡ ልቦናዎት ቢያውቅም ማንፀባረቁ አደጋ ስለሚያስከትልቦት ባይበልጦትም የሚበልጦት እንዲመስለው ይፍቀዱለት፡፡

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1827#sthash.M7CGPknR.dpuf

ከፍቅረኛህ የፍቅር ቦነሶችን ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ይሄንን አንብብ

Posted by tenadam on October 1, 2013 // 25 Comments

·          

·          

·          

·         15

 

EmailShare

የምታፈቅራትን ሴት ለማግኘት ያልወጣኸው ዳገት ያልከፈልከው መስዋዕትነት የለም ይሆናል፡፡ የወንዶች ትልቁ ችግር ታዲያ የሚያፈቅሯት ሴት አጠገባቸው ሆና አብረው ጥሩ ሆነው ጊዜያቸውን እያሳለፉም ስለቀጣዩ የፍቅራቸው ቀጣይነት ብዙ አለማሰባቸው ነው፡፡ በዛችው ቅፅበት ብቻ በሚያሳልፉት ህይወት እርካታቸውን ጣሪያ ላይ በማድረስ ነገስ ስለሚለው የሚያስቡት ነገር በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያፈቅሯትን ሴት ከእጃቸው እንድትወጣ የማድረግ አጋጣሚው ሰፊ የመሆን እድል ይኖረዋል፡፡ ‹‹ሴቶች ምን ይፈልጋሉ›› የሚለው ጥያቄን ሁል ጊዜ ለራስህ እየጠየክና መልስ እየሰህበት ስትመጣ ቀጣይነት ያለው ፍቅርን እያደስክ መምጣት ትችላለህ፡፡ ነገሩ ግን እዚህ ላይ አያበቃም፡፡ ያወቅነውንና መደረግ ያለበትን ጊዜውንና ሁኔታዎችን አመቻችተን መተግበር መቻል አስፈላጊ ነው፡፡ ከእሷ የምናገኘው መረጃ ለፍቅራችን ቀጣይነት እስከጠቀመ ድረስ በተግባር መገለፁ የግድ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ሴቶች ምን ይፈልጋሉ የሚለውን ማወቅ ከዛም መልስ መስጠትና በተግባር መግለፅ የምታፈቅራትን ሴት በእጅህ እንድታስገባት ብቻ ሳይሆን እንድታቆያትም ወሳኝ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ምናልባት በየጊዜው ስለሴቶች ፍላጎት ለማወቅ በጣርክ ቁጥር የማያልቁ ብዙ ፍላጎቶቻቸውን እንደዛውም ብዙ መልሶችንም ልታገኝ ትችላለህ፡፡ አንተ ግን ወሳኝ የምትላቸውን ነገሮች በየዕለቱ ምረጣቸው በተግባርም አውላቸው፡፡ እንደ ጋራ ስሜት በሴቶች ላይ ሊንፀባረቁ የሚችሉ ወሳኝ ፍላጎቶቻቸው ቀጥለው ያሉት ናቸውና እወቃቸው ከዛም ተግብራቸው፡፡ በእነዚህም ሴት ልጅን ካፈቀርካት በኋላ ያንተ ሆና እንድትቆይ ምን ማድረግ እንዳለብህ የሚጠቁምህ ይሆናል፡፡

1. እወቃት
ይህ የመመሪያው ትልቁ የቤት ስራህ ነው፡፡ ቀላል ጉደይ ግን አይደለም፡፡ በተለይም በሀገራችን ባለው ባህል ይህ ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ሴቶችን እያወቅናቸው አላደግንምና፡፡ ሴቶች ግን በተቃራኒው ወንዶችን የማወቅ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ወንዱ ለምን ተከፋ፣ በህይወቱ መስራት የሚፈልገው ምንድን ነው፣ ስለሚበላውና ስለሚጠጣው ሁሉ ሳይቀር ሴቶች በቀላሉ የማወቅ እድል አላቸው፡፡ ይህም ሴቶች ስለወንዱ የማወቅ ጉጉታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡ ይህን የማወቅ ጉጉት አንተም ውስጥ እንዲፈጠር አድርገውና ተግብረው፡፡ በአጠቃላይ የምታፈቅራትን ሴት በትክክል ማወቅህ እርካታዋን ለመጨመር ያግዝሃል፡፡ በቀላሉ ለመግለፅ እርሷን በደንብ ማወቅና የውስጧንም መረዳት በጣም ቀላል የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ማወቅና የውስጧን መረዳት ነው፡፡

2. አፍቃሪ ሁን
ሴቶች ጥሩ ወሲብ ፈፃሚን ብቻ አይደለም የሚፈልጉት፡፡ ጥሩ አፍቃሪ ወንድንም ጭምር እንጂ፡፡ ሴቶች ቅርርብን የሚፈጥር፣ ፍቅርን ሰጥቶ የሚቀበል፣ መንከባከብ የሚችል፣ ነቃ ያለ (እርጋታን ጨምሮ) የሚግባባና ተጫዋች የሆነ እንደዚሁም በግልፅ ስሜቱን የሚገልፅ ወንድን ይወዳሉ፡፡ ይህን እየወደዱልህ ግን አንድ ደረጃ ቀድመህ ሄደህ ፍላጎታቸውን እንድታውቅላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ነገሮችህን መውደዳቸውም ለእነሱ ቀላል የሆንክና መፍትሄ የምትሰጣቸው እንደሆነ ስለሚያስቡ ነው፡፡ ታዲያ አፍቃሪ ሁን ስትባል ሁል ጊዜ አበባና ቸኮሌት ይዞ መምጣት (የፍቅር መግለጫ መሆናቸው እንዳለ ሆኖ) ብቻ ወይንም ስለ እሷ እያሰብክ ብቻ ግጥም ጽፈህ አንብብላት ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ማድረግ ከቻልክ ሳይደጋግሙ እንደ ሁኔታው እነዚህን ማድረጉም መጥፎ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን አሁን እያወራን ያለነው ቀላልና ወሳኝ ስለሆኑና በቀን በቀን አፍቃሪነትህን የበለጠ ስለምታሳይባቸው ነገሮች ነው፡፡ ዋናው አፍቃሪነትህን የሚያሳይልህ የእርሷን ህይወት መጋራት እና እሷን መቅረብህ ነው፡፡ በችግሮቿም ሆነ በደስታዋ ከጎኗ ሁን ልክ እንደ ጓደኛ፡፡ ይህ የበለጠ መቀራረብን ያመጣል፡፡ መቀራረብ ደግሞ አንተን የመፈለግ ዝንባሌዋን ይጨምረዋል፡፡ ታዲያ አንተ ሁልጊዜ ለእሷ ጥሩ ሰው ብቻ ሳትሆን ጥሩ አፍቃሪም መሆንህን በተለያዩ መንገዶች ማሳየት አለብህ፡፡

3. ማድረግ ያለብህን አድርግ
አብራችሁ የመሆን እድልን ባገኘህ ጊዜ የእሷ ኃላፊነት የሆኑ ስራዎችን ተጋራት፣ በመተጋገዝ ለመስራት ሞክሩ፡፡ በነገሮቿ ውስጥ እያገዝካት ስትመጣ የበለጠ የተፈለገችና የተወደደች እንደሆነች ይሰማታል፡፡ በዚህም ለቀጣይ ፍቅራችሁ ራሷን ዝግጁ እደረገች እንድትመጣ ታደርጋታለህ፡፡
ሁል ጊዜም ራስህን ንፁህ አድርገህ ቅረብ፡፡ መስብዕነትን ፍጠርባት፡፡ ሁኔታዎችህ ሁሉ ጥንቃቄህን፣ ማራኪነትህን፣ አማላይነትህንና ተንከባካቢነትህን የሚያሳዩ አድርጋቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ለሴቶች ቅርብ እንደመሆናቸው መጠን እርካታቸውን ይጨምራል፡፡ ከእሷ ነገሮች በመነሳት ነገሮችን እየፈፀምክ በመጣህ ቁጥር ደግሞ ለእሷም ፍላጎት ምላሽ እየሰጠህ እንደሆነ ይሰማታል፡፡ እነዚህንና የመሳሰሉትን ማድረግ እንዳለብህ ካመንክ አድርጋቸው፡፡ ይህንን ስታደርግ ግን እርሷ አድርግልኝ ብለህ ሳይሆን በራስህ ተነሳሽነት መሆን አለበት፡፡ እርሷ ሳትጠይቅህ ካደረክላት ላደረከው ስራ ተጨማሪ የፍቅር ቦነስ የማግኘት እድልህ ይጨምራል፡፡ ይህ ደግሞ ያደረከው ነገር ለእሷ ስትል መሆኑን፣ ምን ያህል እንደምትወዳት እና እንደምትንከባከባት እንድታውቅ ማድረግም ጭምር ነው፡፡ እያንዳንዱን ነገር ስታደርግ ግን በውስጥህ ስሜታዊ የሆነ የወሲብ ስሜት ሊኖርህ አይገባም፡፡ ብዙዎቻችን ሴቶችን ስንቀርብ በችኮላ ነገሮችን ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚወስድብን ቅራኔ ውስጥ የሚከተን በውስጣችን ቅጽበታዊ የወሲብ ስሜት ስሚኖር ነው፡፡ ይህ ከሆነ ያፈቀርካት ሴት አንተ ወሲብ ፈላጊ እንጂ እውነተኛ አፍቃሪ መሆንህን አታውቀውም፡፡ ስለዚህም እነዚህ ነገሮችህ ላይ ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባሃል፡፡ ሁል ጊዜ ማድረግ ያለብህ ነገሮች ሁሉ የፍቅር ሰው መሆንህን የሚያሳዩ ይሁኑ፡፡

4. እርካታና ትኩረት
ሴቶች እርካታን ከማንም በላይ ይፈልጋሉ፡፡ በሁለታችሁ መካከል ጥሩ መቀራረብ የፈጠረው ግንኙነት እየጠነከረና እየረዘመ በመጣ ቁጥር አንዳችሁ ለአንዳችሁ የምትከፍሉት መስዋእትነትም አብሮ ያድጋል፡፡ ያ ማለት ደግሞ በመስዋእትነት የተፈተነና ወደ ጥልቅ ፍቅር የሚያመራ መቀራረብ ይሆናል፡፡ ይህ በመስዋዕትነት የተፈተነ መቀራረብና ፍቅር ደግሞ በእርካታ የተሞላ ይሆናል፡፡ ሴቶችን በሚፈልጉት ነገር ለማርካት ደግሞ እነሱን ማወቅ የመጀመሪያው ስራ ይሆናል፡፡ በመቀጠልም ፍላጎቷን አውቀህ እርካታዋ ሊያሟሉ የሚችሉ ነገሮችን በማድረግ ለማስደሰት ቅርርባችሁን የበለጠ ማጠናከር ነው፡፡ ከላይም የጠቀስናቸው ነገሮች በሙሉ ከእሷ እርካታ ጋር የተያያዙ ናቸውና የእሷን እርካታ የራስህ እርካታ እንደሆነ ቁጠረውና እሷን ለማርካት ሁል ጊዜ መጣር ይገባሃል፡፡
ታዲያ ከእርካታ ጋር በተያያዘ መነሻ የሚሆንህ ለሴቷ የምትሰጠው ትኩረት ነው፡፡ ከአንዲት ሴት ጋር ገና እንደተዋወቃችሁ ሁለታችሁም ብዙ ታወሩ ይሆናል፡፡ አንተ ተናጋሪ ሆነህ እሷ አድማጭ ልትሆን ትችላለች፡፡ ወደ ፍቅር ውስጥ ለገባ ቅርርብ ግን ይህ የተሳሳተ ሂደት ውስጥ ይከተዋል፡፡ ምክንያቱም በተለይም ፍቅር ውስጥ ከገባህ በኋላ አንተ ብዙውን ጊዜ አድማጭ ሆነህ እሷ ስትናገር መስማት አለብህ፡፡ ምን ያህል ትኩረት እንደሰጠሃትም የምትረዳበት መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም ሴቶች አንተ ውስጥ ትልቁን እርካታ የሚያገኙት ጆሮን ስትሰጣቸው ነው፡፡ ሴት ልጅ እንድታዳምጣት በጣም ትፈልጋለች፡፡ የውሸት መስማት ብቻ ሳይሆን ከልባችን የሆነ ማዳመጥን ይፈልጋሉ፡፡ እሷ የምታወራው ምንም ይሁን ምንም ማዳመጥ ተገቢ ነው፡፡ ምናልባትም የምታወራው ቀላልና ብዙ የማይስብ ወይንም ለግንኙነታችሁ የማይጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የምናፈቅራትን ለማግኘት ማዳመጥ ተገቢ ነው፡፡ የአንተ ስራ ታዲያ እርሷ ስታወራ አይን አይኗን መመልከትና ሙሉ ትኩረትህን ወደ እሷ ማድረግ ነው፡፡ ሴቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው የውስጥ ስሜታቸውን የሚያዳምጣቸው ወንድ በጣም ይመቻቸዋል፡፡ ይህም ባላችሁ ግንኙነት ውስጥ ከሁሉም ነገር በላይ (አንተ ማውራት ከምትፈልገው ነገርም በላይ) ትኩረት የሚሰጣቸው ወንድ ምን ያህል ጊዜውንም መስዋዕት እንዳደረገላቸውና ፍላጎቶቻቸውንም እንዳስቀደምክላቸው ስለሚያስቡ ምስጋና ብቻ ሳይሆን ሊሰጡት የሚፈልጉት ብዙ ነገር ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ ፍቅራቸውን መለገስ ዋናው ይሆናል፡፡ በፍቅር ውስጥ ላሉት ደግሞ የበለጠ ፍቅርን እንድትሰጠው ያደርጋታል፡፡ ለራሱ የፍቅር ቦነስ ፈጠረ ማለት ነው፡፡

5. አድናቆትና የፍቅር ቃላት
የምናፈቅራትን ሴት ለማግኘት በሚኖረን ቅርርብ ውስጥ የፍቅር ቃላትን መጠቀም የግድ ነው፡፡ ምን አይነት የፍቅር ቃላትን በምን አይነት ጊዜ መጠቀም እንዳለብህ አስቀድመህ ባታውቅ እንኳን ስለ እሷ ስታስብ ለማወቅና እንዴትስ መጠቀም እንዳለብህ ራስህን ልታዘጋጅ ይገባሃል፡፡ ለምን ቢባል ሴቶች በተፈጥሯቸው በመደነቅ ውስጥ ያለን የፍቅር ቃላትን ይወዳሉ፡፡ የፍቅር ቃላትን ልትጠቀምባቸው ከምትችላቸው አጋጣሚዎች መካከል ቆንጆ እንደሆነች በመናገር መግለፅ ነው፡፡ የምታፈቅራትን ሴት እሷ አንተን እንደምትስብህ መስማት ትፈልጋለችና ስታገኛት ቆንጆ መሆኗን ንገራት፡፡ በተለይም የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿን ለምሳሌ ዓይንሽን፣ ፀጉርሽ፣ ጥርስሽ፣ ቆዳሽ የመሳሰሉትን ለይተህ እየጠቀስክ በጣም ያምራል/ሉ በላት፡፡ እንደዚሁም አለባበሷ፣ አረማመዷ፣ አመለካከቷ፣ የተቀባችው ሽቶ የመሳሰሉት ውበቷ እንዳሰመጠህና እሷን በማሰብም መብላት መጠጣትም እንዳልቻልክ ሹክ በላት፡፡ ታዲያ ስለ ቁንጅናዋ የነገርካትን ሁሌም ያለማቋረት መስማት ትፈልጋለች፡፡ ግንኙነታችሁን እንደጀመራችሁ ሰሞን ወይም እንድትደሰትና ከአንተ ጋር እንድትሆን ስትፈልግ ብቻ ከሆነ የምትነግራት የማድነቅህ ነገር ለዘላቂ መቀራረባችሁ ጥቅም አይኖረውም፡፡ ለምን ሁሌም ቢሆን ሴቶች ይህን የአድናቆት ሁኔታ መስማት ይፈልጋሉ፡፡ ምቾታቸውን ከሚያሳጣ ነገር የማውጣትና ወደ ምቾትና ደስታ የመክተት ኃይል አለውና እነሱን ማድነቅና ማሞካሸት የሁል ጊዜ ስራህ ይሁን፡፡ ከአድናቆት ጋር አያይዘህም ድንቅ የፍቅር ቃላትን እየተጠቀምክ ወደ ፍቅር ዝንባሌ ውስጥ እንድትገባ አድርጋት፡፡ ስትጨዋወቱም ‹‹አንቺን ስላወቁሽ ከልቤ ደስተኛ ነኝ፣ አንቺ በጣም ታውቂያለሽ፣ ሳይሽ በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ነገር ማድረግ የምትችዪ ትመስይኛለሽ›› ስትላት አንተን ከመሰለ ወንድ መለየት እንደማትፈልግ ውስጧ ይደመድማል፡፡ ቀኗን ጠብቅላት እንጂ ነገሩን አፈንድታው ትነግርሃለች የበለጠ የፍቅር ሽሚያ ውስጥም ትከትሃለች፡፡ ሌላ የፍቅር በነስ ማለት ይሄ ነው፡፡
ታዲያ ይህን የፍቅር ቲፖች ጀባ ብትላት እሷም በፍቅር ቦነሶቿ ታስደስትሃለች፡፡ በፍቅር ሽሚያ ውስጥም ሰምጣችሁ ትዋኛላችሁ፣ መልካም ፍቅር!

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1415#sthash.FMDHB8E9.dpuf

ስለተቃራኒ ፆታ መሳሳም ይህን ያውቁ ኖሯል?

Posted by tenadam on August 8, 2013 // 13 Comments

·          

·          

·          

·         0

 

EmailShare


ኡመር ታፈሰ ከአፕል ቫሊ
- መሳሳም 29 የፊት ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል
- ፍቅረኛሞች ሲሳሳሙ ቅባቶች፣ ማዕድን ያላቸው ጨዎችንና ፕሮቲኖችን የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮች ያሉበትን ምራቅ ይለዋወጣሉ፡፡ የቅርብ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መለዋወጥ የሰውነትን በሽታ የመቋቋም አቅም ከፍ ያደርጋል፡፡
- በመሳሳም ወቅት 66 ፐርሰንት የሚሆኑት ዓይናቸውን ይጨፍናሉ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በፍቅረኞቻቸው ፊት ላይ የሚፈጠረውን የደስታ ስሜት በማየት እርካታን ያገኛሉ፡፡
- በአሜሪካ በተከናወነው ጥናት መሰረት አንዲት አሜሪካዊት ሴት ከማግባቷ በፊት በአማካይ ከ80 ወንዶች ጋር ትሳሳማለች፡፡
- ከንፈር ላይ ያለው ስሜት የእጅ ጣቶች ላይ ካለው ስሜት 200 እጥፍ ይበልጣል፡፡
- ወደ ስራ ሲሄዱ ቻው በማለት የሚስቶቻቸውን ከንፈር የሚስሙ ወንዶች ይህን ከማያደርጉ ወንዶች ተጨማሪ አምስት ዓመት የመኖር እድል አላቸው፤ የሚስቶቻቸውን ከንፈር የማይስሙ ባሎች ለትራፊክ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው፡፡
- መሳሳም ሴትን ዘና እንድትል በማድረግ ከጭንቀት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ያስወግድላታል፡፡
- በአማካይ አንድ ሰው በህይወቱ ሁለት ሳምንታትን በመሳሳም ያሳልፋል፡፡
- በዚህች ምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው የመጀመሪያው የፍቅር መሳሳም 14 ዓመት ዕድሜው ላይ ከመድረሱ በፊት የተፈፀመ ነው፡፡ S

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1369#sthash.0w2Rab4o.dpuf

 

ምርጥ የፍቅር ቅመሞች! ወንዶች ብቻ ቢያነቡት ይመረጣል

Posted by admin on May 11, 2013 // 28 Comments

·          

·          

·          

·         8452

 

EmailShare

1. እንክብካቤ አብዛበት
የትኛዋም ሴት ብትሆን ከወንድ ልጅ የሚደረግላትን እንክብካቤ አትጠላውም፡፡ ዓይን አፋር ሴት ደግሞ በማፈሯ የተነሳ ከብዙ ሰዎች የመራቅ ዝንባሌዋ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አንተ ፍፁም የሆነ እንክብካቤ ልታደርግላት ይገባል፡፡ እንክብካቤ እያደረክላት ስትመጣ ለካ ወንድ ልጅ እንዲህ ያስብልኛል ልትል ሁሉ ትችላለች፡፡ በዚህም የመጀመሪያውን ጥያቄ በውስጧ ማሰላሰል ትጀምራለች፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣይነት ለምታደርገው ነገሮችህ የልቤን መንገድ አስቀድመህ የምታንኳኳበት ይሆናል፡፡ ስለ እሷ ባሰብክና በተጨነቅላት ቁጥር ምንም ይሁን ምን ስለአንተ ሁኔታ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ የፍቅርን ምንነት በአንተ እንክብካቤ መነሻነት እንድታውቀው ያስገድዳታል፡፡ ስለዚህም አንተን ፈጽሞ የማትለይበት አይነት እንክብካቤ አድርግላት፡፡
2. ስለ ሌሎች ሰዎች የፍቅር ህይወት አጫውታት
ዓይን አፋር ሴት ራሷን ከብዙ ነገር እንደማራቋ መጠን ከፍቅር ጋር ያላት ግንዛቤም የቀነሰና ጥሩ አመለካከት ላይኖራት ስለሚችል ስለ ፍቅር ምንነት በቀልድና በጨዋታ እያዋዛህ ለማሳወቅ ሞክር፡፡ በተለይም ነጻና ዘና የምትልበትን ጊዜ ጠብቀህ የተለያዩ ሰዎችን የፍቅር ታሪክና አስደሳች የፍቅር ህይወታቸውን አጫውታት፡፡ እዚህ ጋር በቃ አንተ ፍፁም የፍቅር አስተማሪዋ እንደሆንክ መንገዶችን አመቻች፡፡ ከዚህ በፊት የነበራትንም ህይወት ለማወቅ በቀስታ እያወጣጣሀት ታሪኳን ለማወቅ ሞክር፡፡
3. ደስ የሚል ጊዜን አብራችሁ ለማሳለፍ ሞክር
የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ወጣ ባለ መልኩ ከእሷ ጋር መዝናናትና መደሰትን ተግብረው፡፡ በእያንዳንዷ አስደሳች የመዝናኛ ሰዓቶቹ አንተ አፍ አውጥተህ ከምትናገረው ይልቅ የውስጥህን ምኞት ነገሮችህና እንቅስቃሴዎችህ እንዲያሳውቃት አድርግ፡፡ አስደሳች ጊዜን እያሳለፋችሁ ስትመጡ ዓይን አፋርነቷን እየተወችው ስለ አንተ ፍቅር አቀራረብ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ስለዚህም ባገኘኸው አጋጣሚ ይህን ለመተግበር የእሷን አመቺ ጊዜ ልትጠብቅ ይገባሃል፡፡
4. የሚያስደምሙ ስጦታዎችን አበርክትላት
ከአንተ ጋር ያለች ሴት ዓይን አፋርና ለወንድ ልጅ በፍቅር በቀላሉ የማትሸነፍ ከሆነች በጣም የሚማርኩ ስጦታዎችን በተለይም የተለያዩ በዓላትንና የልደቷ ቀንን ጠብቀህ ስጣት፡፡ ስጦታዎችህ በራሳቸው የውስጥህን ፍላጎት የሚናገሩልህ አድርገህ ምረጣቸው፡፡ ስትመርጣቸው ግን የእሷንም ፍላጎት የጠበቀና በጣም ሊያስደስታትና በመደምም ሌላ ነገር እንድታስብ የሚያደርጋት ይሁን፡፡ ታዲያ ስጦታዎችህን መሳሪያ አድርገህ በውለታ ፍቅሯን ለማግኘት እንዳይሆን ተጠንቀቅ፡፡ ይልቁንስ ስጦታዎችህ የውስጥህን ስሜትና ፍላጎት ከማሳወቅና የመልካም ነገር አቅርቦትህ ብቻ እንዲሆኑ ልታውቅም ልታሳውቃትም ይገባል፡፡ ያኔ የአንተን ማንነት የበለጠ ትረዳለች፡፡ ሳትወድ በግዷም ዓይን አፋርነቷ የበለጠ ሊጎዳት ስለሚችል ያንተን ዕድል ልታሳልፍ አትችልም፡፡
5. የጓደኛነት አቀራረብህን ቀይርባት
እሷን ከማወቅህ ጀምሮ ያሉ አቀራረቦችህን የጓደኝነት ወይም ደግሞ የወንድምነት መምሰሉ እየበዛ ሲመጣ አንተን እየጎዳህ ስለሚመጣ ጊዜውንና አመቺ ሁኔታዎችን አይተህ ወደ ፍቅር ፈላጊነት ራስህን ልትቀይርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከአንተ ስለ ፍቅር ምንነት እንደዚሁ በመቅረብህ ብቻ እያገኘች እንጂ በአንተ ልብ ውስጥ ፍቅር መፈለጓን በደንብ ላትገነዘበው ትችላለች፡፡ ምክንያቱም የዓይን አፋር ሴቶች መገለጫ ነውና፡፡ ልቧን በማትጠብቀው ሁኔታ ፍፁም በፍቅር አስደንብረው፡፡ በፍቅር የደነበረ ልብ ደግሞ ልጓሙና መያዣው በአንተ እጅ ውስጥ እንዲሆን አድርገው፡፡
6. ፍፁም አማላይ ሁንባት
የተለያዩ የፍቅር መግቢያ ቴክኒኮችን እየተጠቀምክ በመጣህ ቁጥር አንተ የፍቅር አማላይነትም አብሮ የሚታይ ነው፡፡ ነገር ግን ራሱን በቻለ መልኩ አማላይነትህ በየጊዜው እንዲታያት አድርግ፡፡ የፈለገ ዓይን አፋር ብትሆንም እንኳን የአንተ የአማላይነት አቀራረብህ ውስጡን ሊገዛው ይችላል፡፡ አንተ ያለምንም ፍራቻ በቀረበችህ ሰዓት ደባብሳት፣ እጇን ጭምቅ እያደረግክ ያዛት፣ አሳሳሞችህ ደስ የሚላትና የምትናፍቀው አይነት አድርግባት፣ እያቀፍካት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እየሳምካት ፍቅር ውስጥ ክተታት፡፡ ነገር ግን አሁንም የዓይን አፋርነቷ ባህሪይ ስለሚታወሳት ፀባይዋ ሊለዋወጥ ስለሚችል ሰው በተሰበሰበበት ልትስማትም ሆነ ልታቅፋት አትሞክር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የምታደርጉት ነገር ምንም እንዳልሆነ በራስ መተማመንም እንድታዳብር አድርጋት፡፡ ይህን መፈፀም ከቻልክ ልቧ ውስጥ ትልቅ ፍቅር ማስቀመጥ ተችላለህ፡፡
7. በፍቅርህ ክንፍ እንድትል አድርግ
ከላይ ያሉትን ሁሉ ከተገበርካቸው አንተ በቃ የፍቅር ሰው ነህና ፍቅር መስጠት ተችላለህ፡፡ ታዲያ ፍቅርህን ስትሰጣት እሷንም በአንት ፍቅር ክንፍ እንድትል አድርጋት፡፡ በፍቅር የነካካኸውና የቆሰቆስከውን ልቧን መጋረጃና ማረፊያው አንተው ጋር እንዲሆን አድርግክ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ታዲያ የምን ማፈር ማለት ትጀምራለች፡፡ ምክንያቱም በአንተ የፍቅር ሰው መሆን አይን አፋርነቷን ገልጠህላታልና አንተ የእኔ ‹‹የፍቅር ላምባዲናዬ›› ነህ ማለት ትጀምራለች፡፡ ከዚህ በኋላ ድንቅ የፍቅር ሽሚያ ውስጥ ታስገባትና እሷው ፍቅር ላስተምርህ ሁሉ ማለት ትጀምራለች፡፡ ፍቅራችሁም በምሽት እንደጨረቃና ከዋክብት በቀን ደግሞ እንደ ፀሐይ እየበራ ይታያቸዋል፡፡ መልካም ፍቅርS

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1261#sthash.ZTSaIYa5.dpuf

ፍቅረኛዬን የሚያስቸግራት ሰው አለ

Posted by admin on February 27, 2013 // 14 Comments

·          

·          

·          

·         3326

 

EmailShare


ውድ ደበበ፡- ምን ማድረግ እንዳለብህ የምነግርህ ከዚህ በታች ያለውን ጥያቄ ስትመልስ ነው፡፡ ለመሆኑ ፍቅረኛህ በእርግጥ ትወደኛለች ብለህ ታስባለህ? ለምን ስላንተ ሳይሆን ስለ አለቃዋ ስሜት መጎዳት የምትጨነቅ ይመስልሃል? በመ/ቤቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታስ በየጊዜው እየመጣች ላንተ የምትነግርህ ለምንድን ነው? ለማስቀናት ነው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በጥሞና አስበህባቸው ለመመለስ ሞክር፡፡
በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ ፍቅረኛህ ለምን ስለ ራሷ ተፈላጊነት ብቻ ስታወራ ላንተ ስሜት እንደማትጨነቅ ጠይቃት፡፡ በእርግጥ ብዙ ሴቶች በፍቅረኞቻቸው ወይም በባሎቻቸው የመረሳት ወይም የመተው ስሜት እንዳይሰማቸው በሌሎች ወንዶች እንደተፈለጉ አድርገው ማውራት ይቀናቸዋል፡፡ የምትወድህና አንተ እንዳልከው ወደ ፊት አብራህ በትዳር ለመኖር ሀሳቡ ካላት ግን አንተን ለማስቀናት አትሞክርም፡፡ በዚሁ ድርጊት መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ግን ከአለቃዋ ጋር ከማስቸገር የዘለለ ግንኙነት አላት ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምክንያቱም አለቃዋ አንተን ከተዋወቀ በኋላ እንኳን ሀሳቡን ለመቀየር ፍላጎት እንደሌለው ነው የሚታየው፡፡ እሷም አንተን ወስዳ ካስተዋወቀች በኋላ ከአለቃዋ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቆም ነበረባት፡፡ ግን ጭራሽ ፍቅረኛሽን ተይውና አብረን እንሁን እዳላት ነው የነገረችህ፡፡ ይህ ታዲያ ምን ማለት ነው? ግንኙነታቸው በመ/ቤት ደረጃ ብቻ የተወሰነ ላለመሆኑ የራስህን ማጣራት መስራት አለብህ ባይ ነኝ፡፡ ይህንን ካረጋገጥክ በኋላ የራስህን ውሳኔ ለመወሰን ትችላለህ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

- See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/979#sthash.idAOnr3W.dpuf

 

 mesafint dagnew

 

 

  • Facebook Basic
  • Twitter Basic
  • Vimeo Basic

© 2007By Mesafint dagnew MD2 ./All rights reserved

bottom of page